የአየር ጠባይ ለዉጥና ድርድሩ | ጤና እና አካባቢ | DW | 02.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የአየር ጠባይ ለዉጥና ድርድሩ

በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ዩናይትድ ስቴትስን ያላሳተፈ ስምምነት የዓለማችንን የአየር ጠባይ ችግር መታደግ አይችልም።

default

ቀደም ሲል ገና ከመነሻዉ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ አገራት ከየግዙፍ ተቋሞቻቸዉ የሚለቁትን በካይና አደገኛ ጋዞች እንዲቀንሱ የሚደነግገዉን የኪዮቶ ስምምነት አልፈርምም ያለችዉ አሜሪካ ዛሬም የአየር ንብረትን የሚመለከተዉን ረቂቅ ህግ በገዛ አገሯ ለመደንገግ መንገዳገድ ላይ ናት። እንዲያም ሆኖ የተለያዩ ግዛቶች በራሳቸዉ ተነሳሽነት ለየከተሞቻቸዉ ይበጃል ያሉትን ማድረግ ይዘዋል። ባለፈዉ የአዉሮጳዉያን ዓመት የአገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአየር ንብረትን ለመጠበቅና በአገሪቱ የበካይ ጋዞችን መጠን ለመቀነስ ያለመ ህግ አሳልፏል። ባለፈዉ ሳምንትም እንዲሁ በሴኔቱ ዉስጥ አንድ ቡድን የአየር ንብረትን በአግባቡ ለመጠበቅ የሚያስችል ህግ እንዲወጣ እየሞከረ ነዉ። በዩናይትድ ስቴትስ አዲስ የአየር ጠባይ ለዉጥን ለመግታት ያለመ ረቂቅ ህግ ቢኖርም ባይኖርም በአገሪቱ የአደገኛ ጋዞችን ብክለት በመቀነስ ረገድ ያለዉን እንቅስቃሴ የሚመለከተዉ ጥንቅር ይቀጥላል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ