የአየር ንብረት ጉባኤዉ ሂደት | ጤና እና አካባቢ | DW | 07.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የአየር ንብረት ጉባኤዉ ሂደት

ከተጀመረ አንድ ሳምንት ያስቆጠረዉ በሜክሲኮ ካንኩን ከተማ የሚካሄደዉ የተመድ የአየር ንብረት ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይጠናቀቃል።

default

የጉባኤዉ ተሳታፊዎች በከፊል

ጉባኤዉን የምታስተናግደዉ አገር እንደአምናዉ ሁሉ የዘንድሮዉ ድርድር ሊቀመንበር ናት። አምና ዴንማርክ እንደነበረችዉ አሁን ደግሞ ሜክሲኮ። ያለፈዉ ዓመት ድርድር የተጠበቀዉን ያህል ዉጤት ባለማምጣቱ ከዘንድሮዉም ብዙ የሚጠበቅ ባይሆንም፤ በመጪዉ ዓመት ለሚካሄደዉ ጉባኤ ለስምምነት የሚያደርሱ ነጥቦች ይገኙበታል ተብሎ ይታሰባል። ከተለያዩ አገራትም በጉባኤ ለመሳተፍ ወደካንኩን የተጓዙ እንዳሉ ሁሉ ኢትዮጵያዉያን የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎችም ተገኝተዋል። አንድ ሳምንት ያሳለፈዉን የጉባኤዉን ሂደት ጠይቀናቸዋል። ዝርዝሩን ለመከታተል ከታች ማዳመጫዉን ይጫኑ!

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ተዛማጅ ዘገባዎች