የአየር ንብረት ይዞታ በሳይንሳዊ መረጃና በፖለቲካ ውሳኔ መካከል | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 16.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የአየር ንብረት ይዞታ በሳይንሳዊ መረጃና በፖለቲካ ውሳኔ መካከል

የጀርመን ሳይንቲስቶች የአየር ንብረትን ይዞታና ለውጥ የሚጠቁም ፣ በዓለም ውስጥ ወደር የሌለው ግዙፍ ኮምፒዩተር ፣ ሀምበርግ ከተማ ውስጥ ሠርተው ማቅረባቸውን ገለጡ።

default

ከዚህ ቀደም ከተሠራው 60 እጥፍ ፍጥነት ያለው አዲሱ ኮምፒዩተር፣ በማንኛውም የዓለም ክፍል የአየር ጠባይ ይዞታን መርምሮ የሚከተለውን መጠቆም የሚችል መሆኑ ነውየሚነገረው። 35 ቶን የሚመዝነውና 50 ኪሎሜትር ርዝመት ባላቸw3 የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦዎች የሚጠቀመው ኮምፒዩተር፣ «ብሊዛርድ» የሚል ሥያሜ ተሰጥቶታል። ኮምፒዩተሩ፣ በአንድ ሴኮንድ 158 ትሪሊዮን (ቴራ ፍሎፕስ)ስሌት ማከናወን የሚችል ነው። የጀርመን የምርምር ጉዳይ ሚንስትር፣ አኔተ ሻቫን፣ እንዳሉት፣ ብሊዛርድ፣ ለአየር ንብረት ምርምር ብቻ ነው የሚውለው። 35 ሚሊዮን ዩውሮ ወጪ የተደረገበት ኮምፒዩተር (ብሊዛርድ) ካለፈው ዓመት ከሚያዝያ ወር አንስቶ ሥራውን ሲያካሄድ ቢቆይም፣ በይፋ የተመረቀው፣ አሁን በኮፐንሄገን፣ የዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ-ነክ ጉባዔ በመካሄድ ላይ ባለበት ወቅት ነው።

ለምድራችን ግለት መጨመር ፣ የተቃጠለ አየር (CO2)ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለውና መቀነስም እንዳለበት በሰፊው በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት፣ የጀርመን ተማራማሪዎች ፣ የምድር ግለት ሊቀለበስ የሚችልበት ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል አስታውቀዋል።

(ድምፅ)-----

ተክሌ የኋላ/ሒሩት መለሰ