የአየር ንብረት ትንበያ ሂደት እና ጥቅሙ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 20.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የአየር ንብረት ትንበያ ሂደት እና ጥቅሙ

የአየር ንብረት መለዋወጥ ዓለምን እያሰጋ ያለ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። በከባቢ ሙቀት መጠን መጨመር ምክንያት ፤ የጎርፍ፤ የአዉሎ ነፋስ፤ የባህር ላይ ማዕበል አደጋዎች፤ በዓለማችን በተለያዩ ቦታዎች መከሰታቸዉ ነባራዊ ሁኔታ ነዉ። እነዚህን አደጋዎች ለመከላከል፤ እንዲሁም

epa03907451 Indian people walk through heavy rain in district Ganjam in Orissa, India, 12 October 2013. Cyclone Phailin has made landfall on India's south-eastern Orissa state, bringing fierce winds and heavy rains that uprooted trees and power lines. The storm, packing winds around 200 kilometres per hour barrelled in from the Bay of Bengal to make landfall near the coastal town of Gopalpur, Indian Meteorological Department director LS Rathore said. EPA/STR +++(c) dpa - Bildfunk+++

e

ለሰብል ምርት የዝናብ ወቅትን እና ብዛትን አስቀድሞ ማወቁ በበቂ ጥንቃቄ እና ለአመርቂ የሰብል ምርት አስፈላጊነቱን ባለሞያዎች ይናገራሉ። በዓለማችን ላይ የሚከሰተዉ ከፍተኛ የአዉሎ ንፋስ እና የባህር ላይ ማዕበል እንዲሁም ሃይለኛ ዝናብ እና የከባቢ ሙቀት መጠን በቅድምያ እንዴት ነዉ የሚታወቀዉ? ቀስተ ደመናስ ምንድነዉ?

ከሳምንታት በፊት በፊሊፒንስ በሽዎች የሚቆጠር ህዝብን በአንድ ግዜ የጨረሰዉ ሃያን የተሰኘዉ አዉሎ ንፋስ፤ ፊሊፒንስ ከመድረሱ ከቀናቶች በፊት አደገኛ አዉሎንፋስ ወደ ፊሊፒንስ እየገሰገሰ መሆኑን የአየር ትንበያ ባለሞያዎች አስቀድመዉ ተናግረዋል፤ በዚህም ምክንያት ጥንቃቄ በመወሰዱ የዛኑ ያህል የበርካቶች ህይወት ተርፎአል። ግን የዚህ አይነቱ አዉሎንፋስ አደጋ፤ ከባድ ዝናብ መጣሉ፤ አልያም ፀሃያማ፤ ቀን መዋሉ በቅድምያ እንዴት ይታወቃል? በምስራቅ ጎጃም መቸከል ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አድማጫችን አቶ አማኑኤል ከተማ እባካችሁ መልሱን ጠይቁልን ባሉን መሰረት፤ በአዲስ አበባ በብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ፤ በከባቢ አየር ሁኔታ ትንበያ እና ቅድምያ ማስጠንቀቅያ፤ ዳይሬክቶሪት ዳይሪክተር አቶ ደሪባ ቆርቻ እንደሚሉት፤ ዋናዉ ነገር የባህር ላይ ማዕበልም ሆነ አዉሎንፋስ የሚከሰተዉ፤ በባህር ላይ ባለዉ የአየር ግፊት እና የሙቀት ልዩነት ነዉ፤

በቅርቡ ፊሊፒንስን የመታዉ የባህር ላይ ማዕበል እና አዉሎንፋስ በሰዓት እስከ 300 ኪሎ ሜትር እየተምዘገዘገ ወደ ፊሊፒንስ እያመራ መሆኑ ነበር ቀደም ብሎ የተገለጸዉ። እንደ አየር ትንበያ ባለሞያዉ እንደ አቶ ድሪባ ቆርቻ፤ የአየር ጠባይ ቅድመ መረጃ የሰዓታት የቀናት የሳምንታት እና የወራት ሊሆን ይችላል፤

በቅርቡ በሶማሊያ ገሚስ ራስ-ገዝ መስተዳድር ፑንትላንድን በተከሰተ ኃይለኛ አዉሎ ነፋስ ወደ 300 የሚገመት ሰው መሞቱ ተገልጾአል።

አዉሎ ንፋሱና ነፋሱ ያስነሳዉ የባሕር ነዉጥ ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ ከብቶች መግደሉን፥ በርካታ የአሳ ማጥመጃ ጀልባዎችን ጠራርጎ መዉሰዱም ይታወቃል። በተመድ ስር የተዋቀረ በዓለማች ላይ የሚታየዉን የአየር ንብረት የሚከታተል ማዕከላዊ የመረጃ ቢሮ አለም ተብሎአል።

ይህንኑ የአየር ንብረት ተከትሎ የዘወትር አድማጫችን ቀስተ ደመና ምንድነዉ እንዴትስ ይከሰታል ሲሉ ጠይቀዉን ነበር? ቀስተ ደመና የሚፈጠረዉ ፀሐይ ጨረር እና ርጥባማ የአየር ሁኔታ ባለበት ሁኔታ ዉስጥ ነዉ የሚሉት አቶ ደሪባ አብራርተዉልናል። አቶ ድሪባ በከባቢ አየር መለዋወጥ ሰበብ፤በዓለም ላይ የሚታየዉን እንደ ጎርፍ አዉሎንፋስ እና የባህር ማዕበል አደጋን ለመከላከል የከባቢ አየር ሙቀት መጨመርን መከላከል ይኖርብናል

ይላሉ ። አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic