የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ውጤት ሲገመገም | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 11.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ውጤት ሲገመገም

የዘንድሮው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ከቀድሞዎቹ ምርጫዎች እጅግ የተለየ ውጤት ነው የታየበት ። በሀያ ሰባት የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለአራት ቀናት የተካሄደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ በመሀል ቀኞች እና በቀኝ ዘመሞች ከፍተኛ ድል በመጠናቀቁና ድምጹን ሊሰጥ በወጣው ህዝብ ቁጥር አነስተኛነት ከከዚህ ቀደሞቹ ምርጫዎች ይለያል ።

default

የዛሬ ሳምንት ተጀምሮ እስካለፈው ዕሁድ ድረስ በሀያ ሰባቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በተካሄደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ወግ አጥባቂዎች በድል ተንበሽብሸዋል ። በአንፃሩ የብሪታኒያው ሌበር ፣ የጀርመኑ ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ ፤ የፈረንሳዩ ሶሻሊስት ፓርቲ ፣ በታሪካቸው ታይቶ የማይታወቅ ሽንፈት ተከናንበዋል ። ከሰላሳ ዓመት አንስቶ ህዝቡ በቀጥታ ተወካዮቹን በሚመርጥበት በአውሮፓ ፓርላማ የህዝብ ዕንደራሴዎች ምርጫ ታሪክ እጅግ ዝቅተኛ ህዝብ ድምፅ በሰጠበት በዘንድሮው ምርጫ ቀኝ ፅንፈኞችና ፀረ የውጭ ዜጎች ፍልሰት አቋም ያላቸው ፓርቲዎችም ድል ቀንቷቸዋል ።

ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ