የአውሮፓ ፓርላማና የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ይዞታ | ኢትዮጵያ | DW | 23.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአውሮፓ ፓርላማና የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ይዞታ

የአውሮፓ ፓርላማ ባለፈው ሣምንት አጋማሽ ላይ አካሂዶት በነበረ መደበኛ ስብሰባው የአፍሪቃን ቀንድ አካባቢ ሁኔታ አስመልክቶ አንድ ውሣኔ አስተላልፎ ነበር። ውሣኔው የተላለፈው ቀደም ሲል ባለፈው ጥቅምት ወር ወደ አካባቢው ተጎዞ የነበረ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን፣ ኤርትራንና ጂቡቲን ከጎበኘ በኋላ ባቀረበው ዘገባ ላይ በመመርኮዝ ነው።

default

የአፍሪቃ ቀንድ

በፈረንሣይ ከተማ በሽትራስቡርግ ተቀማጭ የሆነው ፓርላማው ባስተላለፈው ውሣኔ በነዚሁ ሃገራት ያለው የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻል፣ ኤርትራና ኢትዮጵያ የድንበር ውዝግባቸውን በስምምነታቸው መሠረት ዕልባት እንዲያስይዙና ጂቡቲና ኤርትራም እንዲሁ ችግራቸውን በሰላም እንዲፈቱ አሳስቧል። የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ የፓርላማውያን እንደራሴና የተልዕኮውን መሪ አላን ሃቺንሰንን በተለይም በኢትዮጵያ ጉዳይ አነጋግሮ ነበር፤ አጠናቅሮ የላከው ዘገባ የሚከተለው ነው