የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የሀምሳ ዓመት ጉዞ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የሀምሳ ዓመት ጉዞ

የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች እና የመሰረታዊ ነፃነቶች ጥበቃ ድንጋጌ አርባ ሰባት አባላት ያሉት የአውሮፓ መማክርት ሸንጎ ካፀደቃቸው እጅግ ጠቃሚ ድንጋጌዎች አንዱ ነው ።

default

የሽትራስቡርጉ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት

በርካታ አውሮፓውያን ፍትህ ሲሹ ፊታቸውን ወደ አውሮፓው ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ማዞር ጀምረዋል ። የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታዎችን በመመልከት ላይ ያለው ሽትራስቡርግ ፈረንሳይ የሚገኘው የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት እ.አ.አ በ1950 የፀደቀውን የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ መሰረት አድርጎ እ.አ.አ በ1959 የተቋቋመ ፍርድ ቤት ነው ። ይኽው ድንጋጌ ቁጥራቸው ወደ ስምንት መቶ ሚሊዮን ለሚጠጋ ዜጎች ብቻ ሳይሆን በአባል ሀገራት ግዛት ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ መሰረታዊ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶችን ለማስጠበቅ የአውሮፓ ምክርቤት አባላት ቃል የገቡበት ዓለም ዓቀፍ ውል ነው ።