የአውሮፓ ዜጎች ወአሜሪካ ለመሄድ 14 ዶላር ሊከፍሉ ነው | ዓለም | DW | 17.08.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአውሮፓ ዜጎች ወአሜሪካ ለመሄድ 14 ዶላር ሊከፍሉ ነው

ወደ አሜሪካ የመግብያ መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሆኑ ሀገራት ዜጎች 14 ዶላር እንዲከፍሉ ሊደረግ ነው። አዲሱ አሰራር ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ገቢራዊ ይሆናል።

default

የአውሮፓ ዜጎች ወደ አሜሪካ ለመሄድ 14 ዶላር ሊከፍሉ ነው

አሜሪካ 36 ሀገራት ተጠቃሚ የሆኑበትና የመግቢያ መረሃግብሯን በተመለከተ አዲስ መመሪያ ማውጣቷ ከአውሮፓ ህብረት ተቃውሞን አስከትሏል። ከዚህ በፊት ወደ አሜሪካ ለስራም ይሁን ለጉብኝት የሚሄዱ የ36 ቱ ሀገራት ዜጎች የሚጠየቁት ምንም ነገር የለም። ከ2008 ወዲህ የአሜሪካ የሀገር ውስጥ የደህንነት መስሪያ ቤት ከእነዚህ ሀገራት ወደአሜሪካ ለሚገቡ ዜጎች አንድ ቅጽ በማዘጋጀት እንዲሞሉ ማድረግ ጀምሯል። ከመጪው መስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ 14 ዶላር ክፍያ እንደሚጀመርም ተገልጿል። የአውሮፓ ህብረት አዲሱን አሰራር በተመለከተ ቅሬታውን አሰምቷል። የአውሮፓ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ማቲው ኒውማን አዲሱን አሰራር አየመረመርን ነው ብለዋል።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic