የአውሮፓ ም/ቤትና ዘረኝነት በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ም/ቤትና ዘረኝነት በጀርመን

ዘረኝነትንና ያለመቻቻል ስሜትን ፣ ጀርመን መታገል እንደሚኖርባት የአውሮፓ ም/ቤት ፀረ ዘረኝነት ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባ፤ በተለይ ወንጀለኞችን በመያዝና ጥፋተኞችን ተከታትሎ ተገቢውን ቅጣት በመስጠት ረገድ ድክመት ይታያል

DFB untersucht Rassismus-Vorwürfe gegen deutsche U-21-Spieler

ብሏል። የአውሮፓው ም/ቤት ፀረ ዘረኝነት ዘገባ ለ 47 ቱ አባል ሃገራት እያጠናቀረ የሚያቀርበው በየ 5 ቱ ዓመት ነው። ኮሚሽኑ ፤ መዘርዝር ጥናቶች ከሚጠቁሙት በላይ ችግሩ የሰፋ መሆኑንም ነው በዘገባው ላይ ያስታወቀው። የዶይቸ ቨለ ባልደረባ ጀኒፈር ፍራቼክ ያሰናዳችውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

የአውሮፓው ም/ቤት ፀረ ዘረኝነት ኮሚሽን ይፋ የቀረቡ መዘርዝር ጥናቶችንና የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች ያቀረቧቸውን ዘገባዎችም መርምሯል። እ ጎ አ በ 2012 ጀርመን ውስጥ ይፋው መረጃ ፣ ግብረ ሰዶማዊ ባሕርይ ይታይባቸዋል ተብለው በተጠረጠሩ 186 ሰዎች ላይ ከጥላቻ የመነጨ እርምጃ ስለመወሰዱ ያብራራል። የፀረ ዘረኝነቱን ጥናት ካካሄዱትና ዘገባውን ካቀረቡት መካከል Francois Sant’Angelo እንዲህ ይላሉ-

«የጀርመን ባለሥልጣናት ፣ ዘረኛ ፣ የውጭ ተወላጅ ጥላቻ ፣ የሰዶማዊ ባሕርይ ጥላቻ ና ተመሳሳይ ሁኔታዎች ሲከሠቱ የመመዝገብና የመከታተል ሥርዓታቸውን ማሻሻል ይኖርባቸዋል። በተጠቀሱ ምክንያቶች ወንጀሎች መፈጸማቸውን በመመዝገብ ማረጋገጥ ተገቢ ይሆናል። ECRI(ኮሚሽኑ) ይህ ልዩ ማሳሳቢያ ነው ብሎ ያምናል። የጀርመንን ባለሥልጣናት ከምናሳስብባቸው ሁለት ጉዳዮች አንዱ፣ የወንጀል ምዝገባውን ሥርዓት በተሃድሶ ለውጥ እንዲያሻሽሉ የወንጀል ድርጊቶችን እንዲከታተሉ ነው።»

ከ 4 ዓመት በፊት አንድ የመንግሥት ያልሆነ ድርጅት ፤ ከመሰል ጾታዎችና ከተቃራኒ ጾታዎች ጋር ፣ የፍቅርም ሆነ ወሲባዊ ትሥሥር ያላቸውን በጠቅላላ 24,000 ሰዎችን በመጠየቅ ያቀረበው የጥናት ውጤት፤ ከሲሦ በላይ የሚሆኑት የጥላቻ ተግባር ተፈጽሞባቸውል።

ወንጀለኞችን ተከታትሎ የመያዝ ክፍተት ብቻ ሳይሆን፤ በወንጀል መርማሪዎች ላይ ከሞላ ጎደል አመኔታ ማጣቱም ሌላው ችግር ነው። ይህ የቀኝ አክራሪው መፍቀሬ ናዚ ማለትም ብሔርተኛው ሶሺያሊስታዊ ሕብረት (NSU)የፈጸመውን ወንጀል በማጋለጥ ረገድ የተፈጸመውን ስህተት ብቻ አይደለም ጉዳዩ የሚመለከተው። ዘረኛ ወንጀል የሚፈጸምባቸው ብዙዎች ሰለባዎች፤ የኮሚሽኑ ዘገባ እንዳብራራው በተለይ ለባለሥልጣናት አያመለክቱም። የዘረኛ ጥቃት ሰለባዎችን ጉዳይ በጥሞና ለመመልከት ነጻ የአቤቱታ ማቅረቢያ ጣቢያዎች ሊቋቋሙ እንደሚገባም ነው ኮሚሽኑ ያሳሰበው።

አድልዎ የሚፈጸምባቸው ሰዎች ፤ መብታቸው የሚከበርበት የተሻለ ሕጋዊ ርዳታ ያገኙ ዘንድ ምኞቱ ነው። የፌደራሉ ፀረ-አድልዎ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክርስቲነ ሉዑደርስ ---

Flash Galerie Fußball und Rassismus

«ለፀረ አድልዎ መ/ቤቱ ፍጹም ጠቃሚ የሚሆነው፤ የመክሰስ መብት ቢሰጠው ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን የወንጀል ድርጊቶችን ለመከታታል ፣ ለእኛ ቀላል አይደለም። እርግጥ ፣ አንዳንድ፣ ለረጅም ጊዜ የአድልዎ ጉዳዮችን ሲከተታሉ የቆዩ መስርያ ቤቶች ያሏቸው አገሮች አሉ። በዚያም ሥራቸው የተሻለ ነው። አንድን ጉዳይ እስከመጨረሻው መከታተል ከተቻለ፤ ውጤቱንም ማወቅ አያዳግትም። እኛ የምንመካው፤ ጉዳያቸው በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተደመደመ በሚነግሩን ሰዎች ነው። »

የፀረ ዘረኝነቱ ኮሚሽን በዘገባው ላይ እንዳስረዳው በወንጀለኛ መቅጫው ደንብም ጉድለት አለ። ለምሳሌ ያህል እ ጎ አ በ 2008 እና በ 2012 ከዘረኝነት በመነሣት ወንጀል በሚፈጽሙ ላይ ከበድ ያለ ቅጣት እንዲሰጥ በፌደራ ክፍላተ ሀገር ም/ቤት (ቡንደስራት)

የቀረበው ሐሳብ ውድቅ መደረጉ አይታበልም። አንቀጽ 130 ላይ፣ ሕዝብን ለእኩይ ተግባር መቀስቀስን የሚመለከተው ይበልጥ መመርመር ይኖርበታል ነው የተባለው። አንቀጹ እንደሚለው፤ የሚያስቀጣው የህዝብን ፀጥታ የሚያደፍርስ ዘረኛ ስድብ ወይም ንግግር ነው። ለዚህ መረጃ ማግኘቱ ብዙውን ጊዜ ከባድ በመሆኑ አሻሚ ቃል መወገድ ይኖርበታል ነው የተባለው።

Anti Islamisierungskongress von Pro Köln

«እርግጥ ነው ምክክርን በተመለከተ አሁንም የሥራ ቡድናችንን ማጠናከር ተፈላጊ ይሆናል። ምርምሩ፣ የጥናት ክፍተቶችን ለማጥበብ፤ አድልዎን በጥልቅ ለመመርመርና ለማጋለጥ ይበጃል። ይህ ከሆነ ግሩም ነው።»

የአውሮፓ ም/ቤት ፀረ ዘረኝነት ኮሚሽን (ከአውሮፓው ኅብረት ጋር የሚያያዝ አይደለም)

የሚያቀርባቸውን ሐሳቦች ለመፈጸም አባላቱ ግዴታ የለባቸውም።ይሁንና በየጊዜው ስለ ዘረኝነት ላይ የሚያቀርበው ዘገባ አያሳስብም ማለት አይደለም። ፍራንሷ ሳንታ አንጄሎ ፤ በ 47 ቱ አባል ሃገራት ያለመቻቻል ዝንባሌ እየተስፋፋ ነው ነው ያሉት።

«እንደምናስበው በጀርመን ያለመቻቻል ስሜት ትንሽ ሳይጨምር አልቀረም። እርግጥ በመላ አውሮፓ የሚታይ ዝንባሌ ነው። በጀርመንም እንዲሁ«!

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic