የአውሮፓ ህብረት የምክር ቤት ምርጫ የመጨረሻ ቀን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ህብረት የምክር ቤት ምርጫ የመጨረሻ ቀን

ጀርመንን ጨምሮ በ 21 የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ዛሬ የአውሮፓ ህብረት የምክር ቤት ምርጫ ሲካሄድ ውሏል። ሌሎቹ ሰባት ሀገራት ደግሞ አስቀድመው አዲሶቹን የአውሮፓ ህብረት የምክር ቤት አባላት ከባለፈው ሀሙስ አንስቶ እስከ ትናንት ቅዳሜ ድረስ መርጠዋል።

ጀርመንን ጨምሮ በ 21 የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ዛሬ የአውሮፓ ህብረት የምክር ቤት ምርጫ ሲካሄድ ውሏል። ሌሎቹ ሰባት ሀገራት ደግሞ አስቀድመው አዲሶቹን የአውሮፓ ህብረት የምክር ቤት አባላት ከባለፈው ሀሙስ አንስቶ እስከ ትናንት ቅዳሜ ድረስ መርጠዋል።  በርካታ ሀገራት እኩለ ቀን ላይ እንዳስታወቁት የምርጫ ተሳትፎው ከዛሬ አምስት ዓመቱ ምርጫ የተሻለ ነበር ።
420 ሚሊዮን የሚሆኑ አውሮፓውያን በዛሬው ምርጫ ድምፅ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል። ለአራት ቀናት በ28ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ሲካሄድ የቆየው የአውሮፓ ህብረት እንደራሴዎች ምርጫ ውጤት ቀኝ ዘመሞች እንዳይበራከቱበት ተሰግቷል።
በ28ቱ ሀገራት በተደረገ መጠይቅ ቀኝ ዘመሞች ከ20 እስከ 23 በመቶ የምክር ቤቱን ቦታ ይቆጣጠራሉ።በተለይ እንደ ጣሊያን እና ኦስትሪያ ባሉ ሀገራት። ብሔርተኞቹ ወደ አውሮፓ የሚደረገው ፍልሰት እንዲቆም እና ስልጣንም ለየሀገራቱ መንግስት እንዲመለስ ይሻሉ። ይህም ሆኖ በየሀገራቱ ያሉ ዋነኛ ፓርቲዎች አሁንም ከፍተኛውን መቀመጫ እንደሚያሸንፉ ተተንብይዋል። በርካታ ህዝብ ያላቸው አምስቱ የህብረቱ ሀገራት ማለትም ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስፔን እና ፖላንድ ህብረቱን የሚወክሉ 348 እንደራሴዎቻቸውን ይልካሉ። ምክርቤቱ በጠቅላላው 751 እንደራሴዎች ይኖሩታል። በዚህ ምርጫ እስካሁን አባልነቷ ያልተቋረጠው ብሪታንያም ተካታለች።  የምርጫው ቅድመ ውጤት ከምሽቱ አራት ሰዓት ገደማ ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።


ልደት አበበ

ተስፋለም ወልደየስ

ተዛማጅ ዘገባዎች