የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ | ዓለም | DW | 22.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ

የዛሬው የ27 ቱ አባል ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ከመጀመሩ አስቀድሞ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ እንደተናገሩት ጉባኤው በግለሰቦችም ሆነ በኩባንያዎች ደረጃ ለሚፈፀመው የታክስ ማጭበርበር እኩል ትኩረት ይሰጠዋል ።


በከፍተኛም ሆነ በዝቅተኛ  ደረጃ የሚካሄደው የታክስ ማጭበርበር ዛሬ ብራሰልስ ቤልጂግ በመካሄድ ላይ ያለው የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ትኩረት ነበር። በፈረንሳይና በጀርመን አንዳንድ ታዋቂ ግለሰቦች ቀረጥ እንዳይከፍሉ ገንዘባቸውን ወደ ሌሎች አገራት ማሸሻቸው በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ከተደረገ ወዲህ የታክስ ማጭበርበር በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ስጥቷል። የዛሬው  የ27 ቱ አባል ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ከመጀመሩ አስቀድሞ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ እንደተናገሩት ጉባኤው በግለሰቦችም ሆነ በኩባንያዎች ደረጃ ለሚፈፀመው የታክስ ማጭበርበር እኩል ትኩረት ሰጥቶ ይነጋገራል። የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ኬምረን ደግሞ የሚጣለው የግብር ወይም የታክስ መጠን የንግድ ድርጅቶች ሥራ እንዲፈጥሩ የሚያበረታታ መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል። ስለ ዛሬው የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የመነጋገሪያ አጀንዳ የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic