የአውሮፓ ህብረት እርዳታ ለአሚሶም | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ህብረት እርዳታ ለአሚሶም

ይኽው ተጨማሪ እርዳታ አሚሶም ተልዕኮውን በሙሉ አቅሙ እንዲወጣ የሚያግዝ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ገልጿል ። ፣ህብረቱ ተጨማሪ እርዳታ የሰጠው የአሚሶም የእስካሁኑ ተግባር አበረታች በመሆኑ ምክንያት ነው ሲሉ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኑነቶች ቢሮ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

የአውሮፓ ህብረት በሶማሊያ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ አሚሶምን ለማገዝ ተጨማሪ 82 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት መወሰኑን ትናንት አስታውቋል ። ይኽው ተጨማሪ እርዳታ አሚሶም ተልዕኮውን በሙሉ አቅሙ እንዲወጣ የሚያግዝ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ገልጿል ። ፣ህብረቱ ተጨማሪ እርዳታ የሰጠው ሶማሊያ ዘላቂ ሰላም እንዲኖራትና እንድትረጋጋ በሚደረገው ጥረት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የአሚሶም የእስካሁኑ ተግባር አበረታች በመሆኑ ምክንያት ነው ሲሉ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኑነቶች ቢሮ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic