የአውሮፓ ህብረት አምባገነኖችና የ HRW ነቀፌታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 25.01.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ህብረት አምባገነኖችና የ HRW ነቀፌታ

መቀመጫውን ኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዎች ባለፈው ዓመት ያቀረበው ዓመታዊ የሰብዓዊ መብት ዘገባ ፣ በዓለም ዙሪያ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፣ ድርጅቶች እና ተቋማት ላይ መብት ጣሽ መንግስታት የሚያደርሱት ጥቃት እየተባባሰ መምጣቱን አጉልቶ ያሳየ ነበር ።

default

Human rights Watch ትናንት ይፋ ያደረገው እ.ጎ.አ የ 2011 ዓ.ም ዓመታዊ ዘገባው ደግሞ የዚህን ችግር ሌላ ገፅታ ለማሳየት የሞከረ ነው ። ዘገባው በዚህ ዓመት ልዩ ትኩረት የሰጠው የሰብዓዊ መብት በማክበር እና በማስጠበቅ ምሳሌ የሚሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና ክፍለ ዓለማዊ ድርጅቶች እንዲሁም ምዕራባውያን መንግስታት ሰብዓዊ መብት የሚጥሱ መንግስታት ላይ ጫና ከማድረግ ይልቅ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በማለፍ ለችግሩ መባባስ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ ላይ ነው ። በዚህ ረገድ HRW የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ፣ የአውሮፓ ህብረትን ፣ ዩናይትድ ስቴትስንና ፈረንሳይን እንዲሁም ጀርመንን በምሳሌነት አንስቷል ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ድርጅቱ በተለይ በአውሮፓ ህብረት ላይ በሰነዘረው ትችት ላይ ያተኩራል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ