የአውሮፓ ህብረት ና ዚምባብዌ | ዓለም | DW | 27.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአውሮፓ ህብረት ና ዚምባብዌ

በውሳኔው መሰረት በ81 ግለሰቦችና በ8 ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የንግድና የጉዞ እገዳ ተነስቷል ። የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ጨምሮ 10 ግለሰቦችና 2 ኩባንያዎች ግን አህንም እገዳው እንደፀናባቸው ይቆያል ።

የአውሮፓ ህብረት በዚምባብዌ ላይ ጥሎት የነበረውን የኤኮኖሚና የጉዞ እገዳ ከትናንት ጀምሮ በአብዛኛው ያነሳ መሆኑን የህብረቱ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ካትሪን አሽተን አስታውቀዋል ። ውሳኔው የተላለፈው በቅርቡ በዚምባብዌ የተካሄደው ህገ መንግሥታዊ ህዝበ ውሳኔ ሠላማዊና ተአማኒ መሆኑን ተክትሎ እንደሆነ ካትሪን አሽተን ያወጡት መግለጫ ያስረዳል ። በውሳኔው መሰረት በ81 ግለሰቦችና በ8 ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የንግድና የጉዞ እገዳ ተነስቷል ። የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ጨምሮ 10 ግለሰቦችና 2 ኩባንያዎች ግን አህንም እገዳው እንደፀናባቸው ይቆያል ። ገበያው ንጉሴ ከብራስለስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic