የአውሮፓ ህብረት ቼክ ሪፐብሊክና ስዊድን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 02.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ህብረት ቼክ ሪፐብሊክና ስዊድን

የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በዙር የሚደርሳቸውን የፕሬዝዳንትነት ስልጣን ስዊድን ትናንት ከቼክ ሪፐብሊክ ተረክባለች ።

default

ስዊድን ሃላፊነቱን የወሰደችው የገንዘብ ቀውስ እና የምጣኔ ሀብት ኪሳራ እንዲሁም ስራ አጥነት አውሮፓን ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ በሚፈትንበት ወቅት ነው ። የቼክ ሪፐብሊክ የፕሬዝዳንት ዘመን እንዴት ነበር ? ስዊድንስ ምን ይጠብቃታል ? የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን አንዱ ትኩረት ነው ።

የኢራቅ ስደተኞች በጀርመን

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኢራቅ ስደተኞች ባለፉት ስድስት ዓመታት በተለያዩ ሀገራት የስደት ኑሮ እየገፉ ነው ። ከነዚህም አብዛኛዎቹ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተጠለሉ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ አውሮፓ ደርሰዋል ። የኢራቅን ስደተኞች ካስጠጉት የአውሮፓ አገራት አንዷ ጀርመን ናት ። ከሶሶት ወራት በፊትም ጀርመን በተባበሩት መንግስታት መርሀ ግብር ስር አራት መቶ የኢራቅ ስደተኞችን ተቀብላለች ። የነዚህ ስደተኞች አያያዝ ምን እንደሚመስል የሚያስቃኝ ቅንብርም አለን ።

ሒሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ