የአውሮፓ ህብረት መስፋፋት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 24.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ህብረት መስፋፋት

በስድስት አገራት የጋራ ፍላጎት ተጠንስሶ የአባላቱ ቁጥር አሁን 27 የደረሰው የአውሮፓ ህብረት ከአሁን በኃላ አዳዲስ አባላትን በሚቀበልበት መንገድ ላይ አባል ሀገራቱ የተለያዩ አቋም እንደያዙ ነው ።

default

አንዳንድ ሀገራት እንደ ቱርክ የመሳሰሉ ረዘም ካለ ጊዜ አንስቶ የአባልነት ድርድር ላይ ያሉ ሀገራት ይታቀፉ ሲሉ አንዳንዶች በተለይም መስራቾቹ ቱርክን በሙሉ አባልነት መቀበል የለብንም የሚለውን ግትር አቋማቸውን በማራመድ ላይ ናቸው ። የአየርላንድን ህዝብ ይሁንታ የጀርመን የቼክ ሪፐብሊክንና የፖላንድን መሪዎች ፊርማ የሚጠብቀው የተሻሻለው የሊዝበኑ የአውሮፓ ህብረት ውል እስኪፀድቅ ድረስ የመስፋፋት ጉዳይ ለጊዜው የተገታም ይመስላል ።

ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ