የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪቃ አቀፍ የልማት እቅድ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 07.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪቃ አቀፍ የልማት እቅድ

ገንዘቡ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በተግባር ለሚውሉ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ እንደሚውል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ትናንት አስታውቋል ።

የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪቃ አቀፍ የእድገት ትብብር የፓን አፍሪቃ መርሃ ግብር የመጀመሪያው ምዕራፍ 415 ሚሊዮን ዩሮ መመደቡን ትናንት አስታውቋል ። ይህ ገንዘብም ህብረቱ እጎአ እስከ 2020 ድረስ ለአፍሪቃ አቀፍ የልማት እቅድ ለመስጠት ከመደበው 845 ሚሊዮን ዩሮ ውስጥ የመጀመሪያው ልገሳ መሆኑ ነው ። ገንዘቡ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ እንደሚውል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ትናንት አስታውቋል ። ባለፈው ሚያዚያ በተካሄደው የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የጋራ ጉባኤ ላይ ነበር የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ሆዜ ማኑዌል ባሮሶ አፍሪቃ አቀፍ የልማት መርሃ ግብርን በይፋ ያበሰሩት ።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic