የአውሮፓው ኮሚሽንና ስደተኞች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 14.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓው ኮሚሽንና ስደተኞች

የአውሮፓው ሕብረት ስደተኞችን የሚያስተናግድበትንና የሚቆጣጠርበትን አዲስ አቅድ ትናንት ይፋ አድርጓል። ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ ፤ ከጥር ወር ወዲህ ብቻ ባሕር ላይ ሰጥመው ያለቁት በሺ ዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ናቸው።

በተለይ ባለፈው ወር በአንድ 900 የሚሆኑ ሰዎች የሰጠሙበትን እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ተከትሎ፤ የሕብረቱ መሪዎች፤ አዲስ መርሐ-ግብር እንዲነደፍ ወስነው እንደነበረ አይዘነጋም። የኮሚሽኑ የትናንት መርሐ ግብርም፤ በዚሁ በመሪዎቹ ስብsmባ በተሰጠው ውሳኔ መሠረት፣ የባሕር ላይ የነፍስ አድኑን መርሐ ግብር ለማጠናከር በሕገ ወጥ አሠራር ሰዎችን ካገር -አገር የሚያሸጋግሩትን፣ ለመቆጣጠር፣ ስደተኞችን በአባል አገሮች በማከፋፈል ፤ በሜድትራንያን ባሕር አዋሳኝ አገሮች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ እንዲሁም ሕጋዊ መግቢያ ሥርዓት በመፍጠር ሰዎች ወደ አደገኛ የጉዞ መሥመር እንዳይገቡ ለማድረግan በረጅም ጊዜም ሰዎችን በየአገራቸው በሚያሳድዱና በሚያፈናቅሉ መሠረታዊ ችግሮች ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ተገልጿል።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic