የአውሮፓው ኅብረትና ልማት-ነክ ፖለቲካው፧ | ኤኮኖሚ | DW | 28.05.2004
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የአውሮፓው ኅብረትና ልማት-ነክ ፖለቲካው፧

ከሚያዝያ ፳፫ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ. ም. ጀምሮ፧ የአውሮፓው ኅብረት የአባላቱን ቁጥር ብቻ አይደለም የጨመረው። ልማት ነክ የፖለቲካ መርኁም አዲስ አወቃቀር አስፈልጎታል። የአውሮፓው ኅብረት፧ በያመቱ፧ ፳፮ ቢልዮን ዩውሮ ማለትም ዓለም በመላ ከሚያዋጣው ገሚሱን ለአዳጊ አገሮች ልማት እንደሚያውል ይነገራል።

፲ አዳዲስ አባላትን በመጨመር፧ አሁን ፳፭ አገሮችን ያቀፈው የአውሮፓው ኅብረት፧ ከ ፻፵፫ አዳጊ አገሮች ጋር የሚኖረው የወደፊቱ ግንኙነት ምን ሊመስል ይችላል? ይህ ርእሰ-ጉዳይ፧ ከጥቂት ወራት ወዲህ ይበልጥ የተተኮረበት ሲሆን፧ ቦን ውስጥ፧ ባለፈው ረቡዕ፧ ፬ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች ባዘጋጁት ስብሰባም ላይ፧ ላቅ ያለ ትኩረት ሳይደረግበት አልቀረም።
በፖለቲካና በሥነ-ፍጥረት ላይ ያተኮሩ፧ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች፧ እንደሚገነዘቡት፧ የልማት ተራድዖው ፖለቲካ፧ በአዲስ መልክ እንዲፈተሽ ማስገደዱ አይቀርም። በጀርመን የልማት ተረድዖ ሚንስቴር፧ ተጠሪ የሆኑት፧ ወይዘሮ Heike Pörksen ስለወደፊቱ የአውሮፓው ኅብረት የልማት እርዳታ ነክ ፖለቲካ፧ እንዲህ ብለዋል።
O-tone( “Sie wird sich eventuell.................... andere Tendenzen”
«ወደፊት ዞሮ ዞሮ፧ በመልክዓ-ምድራዊ አመለካከት ሳቢያ ፧ በከፊልም ቢሆን ለውጥ መከሰቱ የማይቀር ነው። በአሁኑ ጊዜ፧ አዲስ የጉርብትና ፖለቲካ በተሰኘው ጉዳይ ላይ ውይይት ከፍተናል። አዲሶቹ አባላት፧ እ ጎ አ ከ 2007 ዓ ም አንስቶ፧ ከአውሮፓው ኅብረት ገንዘብ የሚቀርብላቸው ሲሆን፧ እስካሁን ከሚያገኙት እጅግ ላቅ ያለ ገንዘብ ያሻቸዋል? ይህ ደግሞ፧ ከታወቁት በመልማት ላይ ከሚገኙት አገሮች ጋር ያለውን ትብብር ክፉኛ ይጎንጠው ይሆን? ጥቂት የሚያሠጋን፧ ይህ ነው። ድህነትን መታገል፧ የጋራ ዓለማ መሆኑ እንዳይዘነጋ እንከታተላለን። ይሁንና በከፊል፧ ሌላ አዝማሚያ መኖሩ ተስተውሏል«።
ከታሪካዊ ተመክሮአቸው በመነሣት ብዙዎቹ፧ አዳዲሶቹ የአውሮፓው ኅብረት አባል መንግሥታት፧ ለራሳቸው የሚያተኩሩባቸው ጉዳዮች ሌሎች ናቸው። ለምሳሌ ያህል፧ የፀጥታ ጥበቃና የኤኮኖሚ-ነክ ፖለቲካ፧ እንዲሁም በአዳጊ አገሮች የዴሞክራሲ ግንባታ፧ በእነርሱ አመለካከት ላቅ ያለ ግምት ይሰጣቸው ይሆናል። በእስሎቫኪያ፧ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች መድረክ መሪ ማሪያን ቻውቺክ፧ አካባቢአቸው ስለሚሰጠው ቅድሚያ ሲያብራሩ፧
O-ton (Die neuen Mitgliedsländer werden mehr mit den Ländern kooperieren........Asien”
«አዲሶቹ የአውሮፓው ኅብረት አባል አገሮች፧ የረጅም ጊዜ ትብብር ካላቸው አገሮች ጋር፧ መተጋገዙን ሳይገፉበት አይቀሩም። በባልካንና በቀድሞዎቹ የሶቭየት ሪፓብሊኮች ትኩረት ይደረጋል። ይሁንና፧ በደቡቡ ንፍቀ-ክበብ የሚገኙ የአፍሪቃም ሆነ የእስያ አገሮችም አሉ«።
ማሪያን ቻውቺክ አሁንም ፧ የአዳጊዎቹን አገሮች ሥጋት እንደሚገነዘቡ በመጥቀስ፧ O-ton(”Meiner Meinung nach wäre es nicht fair,.............EU haben”
«እንደእኔ አመለካከት፧ የአፍሪቃና የእስያ አገሮች፧ በአውሮፓው ኅብረት መስፋፋት ሳቢያ ከ አውሮፓው ኅብረት አኳያ አቋማቸው ይበልጥ የከፋ ቢሆን ፍትኀዊነት የጎደለው ይሆናል«።
ከጀርመን የልማት ታራድዖ ሚንስቴር፧ Heike Pörksen ቀጠል በማድረግ፧
O-ton(”Es gibt sehr starke Füesprecher für Asien und afrika.......passieren wird.”
ለእስያና ለአፍሪቃ እጅግ ጠንክረው ጥብቅና የቆሙ አሉ፧ የአውሮፓው ኅብረት ፍጹም መስተፋጥናዊ በሆነ ለውጥ፧ አቋሙን ይቀይራል ብዬ አላስብም፧ ይሁንና በቀጥታ ለሚያጎራብቱ አገሮች ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን፧ የተፈጥሮ ሀብት መጠን ሲቀንስ ደግሞ የማሸጋሸግ ተግባር መፈጸሙ አይቀሬ ነው። ይህ ሊሆን እንደሚችል መቀበል ይቻላል። አዲሶቹ የአውሮፓው ኅብረት አባል መንግሥታት፧ ከኅብረቱ ጋር ሲቀላቀሉ በእኩል አባልነት፧ ከአውሮፓው ኅብረት የልማት ተርድዖ መርኀ-ግብር ጋር መተሣሠራቸው አይዘነጋም። እርግጥ በአሁኑ ጊዜ የሚያዋጡት ድርሻ፧ ከሞላ-ጎደል ዝቅተኛ ነው። ወደፊት ግን መጠኑ መጨመር ይኖርበታል። ይህም ተፈላጊ ገንዘብ ለማቅረብ ጥረት የሚደረግበት እርምጃ ከባድና ፧ ለአዲሶቹ አባል አገሮች ህዝብ የማይጥም ነው የሚሆነው።