የአውሮፓው ሕብረትና ፤ በስደተኞች የሚነግዱ ቡድኖች | ዓለም | DW | 21.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአውሮፓው ሕብረትና ፤ በስደተኞች የሚነግዱ ቡድኖች

የአውሮፓው ሕብረት ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ሰዎችን ካገር አገር ፤ በተለይም በሊቢያ በኩል ወደአውሮፓ የሚያሸጋግሩትን ለመታገል፤ በሳምንቱ መግቢያ ላይ ፤የውጭ ጉዳይና መከላከያ ሚንስትሮች ባደረጉት ስብሰባ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:37
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:37 ደቂቃ

የአውሮፓው ሕብረትና ፤ በስደተኞች የሚነግዱ ቡድኖች

ውሳኔው እስከምን ድረስ አመርቂ ውጤትም ሆነ መፍትኄ ያስገኛል?የሚጠራጠሩ አሉ ። አንዷ ፣ የጀርመንን አረንጓዴ ፓርቲ በመወከል የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ባርብራ ሎህቢለር ናቸው ።

የአውሮፓ ፖለቲከኞች፤ መገናኛ ብዙኀንም ከሰሞኑ ደጋግመው ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ ከሰሜን አፍሪቃ ፤ በማዕከላዊው ባሕር በኩል ፤ አደገኛ በሆኑ፤ በማያስተማምኑ ጀልባዎችan መርከቦች፤ ወደ አውሮፓ ለመግባት በየጊዜው የሚጥሩ ስደተኞችን ጉዳይ ነው። ሰዎች ለስደት እንዳይነሳሱ፤ በዚያው በሚኖሩበት ሀገር ኑሮአቸው እንዲሻሻል መርዳት ነው የሚበጀው የሚሉ አሉ። ጀልባዎችን ፤ መርከቦችን መደምሰስ መፍትኄ አይሆንም ባዮችም ጥቂቶች አይደሉም። በጭንቅ ላይ በሚገኙ ስደተኞች ትርፍ የሚዝቁ ጨካኝ ቡድኖች ላይ ርምጃ መውሰድም ሆነ በጥብቅ መታገሉ፤ እንዴት ይታያል? ለባርብራ ሎህቢለር የቀረበ ጥያቄ ነበር።

«ዘላቂ ዓላማን ባነገበ መልኩ እነርሱን መታገል ያስፈልጋል። የጭካኔ ተግባራቸውንና ንግዳቸውን ለማስቆም ርምጃ ሊወሰድ ይገባል። ሥራቸውን መቅኖ እንዲያጣ ለማድረግ ከሆነ የፖለቲካው ትግል ፤ ሥልቱ፣ የተለዬ መሆን አለበት። ለምሳሌ ያህል ስደተኞች፣ በሕጋi መንገድ አውሮፓ እንዲገቡ ዕድል መስጠት ይቻላል።»

በ,ው መገለጽም ፤ መደረግም ያለበት? ውሳኔዎች ከአውሮፓ ፓርላማም ሆነ ከአውሮፓው ሕብረት ፤ ለምሳሌ ያህል የመጀመሪያ ደረጃ ርምጃ የተሰኘ ቀርቧል። በቅድሚያ ሁኔታው በሚገባመጠናት አለበት። የአነዚህን ሕገ ወጥ ነጋዴዎች አደረጃጀት ያን ያህል በትክክል የሚያውቅ የለምና!

«ይመስላል! ሊሆን ይችላል፣ እንዴት እንደተቋቋሙ፣ በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተደራጁ መገንዘቡ ያዳግታል። የተደራጀ ኩብለላ የሚባል ነገርም የለም። ብዙዎች ስደተኞች፣ ከቤተሰብ አባላት ጋር ሆነው ነው የሚጓዙት። በHege ወጥ መንገድ ሰዎች አመላላሾቹ በተለዬ መልኩ ነው የተደራጁት። ከፊሉ ሚሊሺያ ጦር አላቸው። ሊቢያ ውስጥ ያሉትን ማለት ነው። አንዳንዶች በተናጠል የሚሰሩ ናቸው።የተደራጁ፤ እንዲሁም አልፎ-አልፎ የሚሠሩ አማተሮች አሉ። እነርሱን መደምሰስ የየሚያስችል ስልት አለ ። አደረጃጀታቸውን ማወቅ አያስቸግርም ማለቱ ማስተዋልን የሚጠቁም አይደለም። »

የጦር ኤይል ርምጃ እንዲወሰድ የተባበሩት መንግሥታት ሥልጣን ይሰጣል? ወይም የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት ውሳኔ አስፈላጊ ነው ወይ? ይሣካ ይሆን?

«እስከመጪው ወር ምናልባት ውሳኔ ላይ ይደርሳል የሚል ግምት አለ። ግን ቀላል አይደለም። ስደተኞች እንደተፋላሚ እንዳይታዩ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል። ምክንያቱም፤ ስደተኞች እስካሁን በፀጥታ ጠንቅ ሆነው አልተገኙምና! የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር፣ አንቀጽ 7 በሚያብራራው መሠረት፣ ሥልጣን የሚሰጠው በፀጥታ ላይ አደጋ የደቀነ ሲገኝ ነው።»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic