የአውሮፓና ጀርመን የ2013 አበይት ክንውኖች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 31.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮፓና ጀርመን የ2013 አበይት ክንውኖች

ዛሬ እኩለ ለሊት የምንሸኘው የጎርጎሮሳውያኑ 2013 በአውሮፓ የሥራ አጡ ቁጥር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ያሻቀበበት ፣ የወጣት ሥራ አጦችን ቁጥር ለመቀነስ የክፍለ ዓለሙ መሪዎች መፍትሄ ይሆናል ያሉትን ያቀዱበት ፣

ከ360 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ የውሃ ሲሳይ ሆነው የቀሩበት ፣ የጀርመን ምክር ቤት ምርጫ ተካሂዶ አዲስ ትልቅ ጥምር መንግሥት የተመሠረተበት በዩክሬን መንግሥት ላይ የተነሳው ተቃውሞ ተባብሶ የቀጠለበት ዓመት ነበር ። እነዚህንና ሌሎችንም የ2013 አበይት ክስተቶች የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ይቃኛቸዋል ።ዓመቱ ሲጀመር የዓለም የገንዘብ ቀውስ ግንባር ቀደም ተጠቂ ግሪክ ተደጋጋሚ የስራ ማቆም አድማ ተቃውሞ የሚያካሂዱት የሠራተኛ ማህበራት የታሰበውን የገቢ ቅነሳ እንዲቀበሉ ማሳሰቢያ ሰጠታ ነበር ። የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዚህ መከራከሪያቸው መንግሥት የደሞዝ ቅነሳን ተግባራዊ ካላደረገ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ከዓለም ዓቀፍ ተቋማት የሚገኙ ብድርና እርዳታዎች ተመናምነው ሃገሪቱን ለክስረት ትዳረጋለች የሚል ነበር ። ከ5 ዓመት ወዲህ የአውሮፓ በተለይም የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት ራስ ምታት ሆኖ የዘለቀው የገንዘብ ቀውስ መዘዝ በ2013 ም የአውሮፓን መሪዎች መልሶ መላልሶ ሲያነጋግግር ሲያነታርክ የከረመ ጉዳይ ነበር ። የአባል ሃገራቱ መሪዎች አውጥተው አውርደው በዓመቱ መገባደጃ ባንኮችወደፊት ሊገጥማቸው የሚችልን ችግር መቋቋም የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋት ተስማምተዋል ። 2013 በ17 ቱ የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት የሥራ አጡ ቁጥር ከመቼውም በላይ የናረበት ዓመት ነበር ። ይህ ደግሞ የመስኩ ባለሞያዎች

እንደተናገሩት ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ነው ። በተለይ ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ የገጠማቸው የደቡባዊ አውሮፓ ሃገራት ፖርቱጋል ስፓኝ ኢጣልያ ና ግሪክ የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሾች ናቸው ። የገንዘብ ቀውሱ ያስከተለው ችግር ይበልጥ የጠናባት ግሪክ በሥራ አጡ ብዛት ቀዳሚውን ቦታ ይዛለች ። አንድ የሃገሪቱ ፓርላማ አባል እንዳሉት ከሁሉም በግሪክ የወጣት ስራ አጥነት ነው የተባባሰው ።« በግሪክ ሁኔታው በእውነት ከሰብዓዊ ጥፋት ጋር የሚነጻፀር ነው ። ሥራ አጥነት እጅግ ከፍተኛ ነው ። ወደ 27 በመቶ ይጠጋል ። የወጣት ሥራ አጥነት ደግሞ 60 በመቶ ነው ። ይህ ፍፅም አዲስ የሆነ ነገር ነው ። ስፓኝም ተመሳሳሳይ ችግር እንዳለባት አውቃለሁ ። »

በአውሮፓ አብይ ችግር በሆነው ወጣት ሥራ አጥነት ላይ በ2013 የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ትኩረት ሰጥተው በመምከር መፍትሄም ቀይሰውለታል ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት እንዳሉት መሪዎቹ የታሰበው ግቡን እንዲመታ የሚያስችል እቅድ ላይ ተስማምተዋል ።

« በአውሮፓ የሚገኙ የሥራ አፈላላጊ ድርጅቶች አንድ ላይ ተሰብስበው በአንድ እቅድ ተሰማምተዋል ። ይህም እጅግ በጣም ጥሩ የሚባል አሠሪና ሠራተኛን ማገናኛ ስርዓት ሲሆን ፣ ሃገራት በሞላ የሥራ ልምድና የተሞክሮ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያበቃ ነው ። »

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎቹ በዓመቱ አጋማሽ ሰኔ ላይ ባካሄዱት ጉባኤ ችግሩን ለመፍታት የሚውል 6 ቢሊዮን ዮሮ ለመመደብ ተስማምተዋል ። ገንዘቡም በአባል ሃገራት መዋጮ እንደሚሸፈን ነው የሚጠበቀው ። አባል ሃገራቱ ከገንዘብ ቀውስ ለመራቅ የወጪ ቅነሳ እንዲያደርጉ ግፊት እየተደረገ ገንዘቡ ከየት ሊገኝ እንደሚችል ግን ማጠያየቁ አልቀረም ።

NSU-Mordopfer Mehmet Kubasik EINSCHRÄNKUNG

የተገደሉት አባት ከቤተሰቦቻቸው ጋር

በጀርመንበህቡዕ ሲንቀሳቀስ የቆየው በጀርመንኛው ምህፃርNSU በመባልበ ሚታወቀው የናዚዎች ቡድንከዛሬ7 ዓመት በፊት አባቷ የተገደሉባት ቱርካዊ ጀርመናዊት ምስክርነትነበር።ቡድኑ ለተጠረጠረባቸው መሰልግ ድያዎች ተጠያቂ ከተባሉትየ አንዷየፍርድ ሂደት የተጀመረው በ2013 በግንቦት ወር ነበር።ቡድኑ እጎአ ከ2000 እስከ 2007 9 የውጭተወላጆችንና1 ፖሊስበተለያዩ የጀርመን ከተሞች በመግደል ይጠረጠራል።NSU ከነፍስ ግድያው ሌላ እጎአ ከ2001 እስከ 2004 ኮሎኝ ውስጥ የባንክ ጥቃቶች በማድረስ 14 የባንክ ዘረፋዎችን በመፈፀም እንዲሁም የውጭ ዜጎችን መኖሪያ ቤቶች በማቃጠልም ተጠርጥሯል ።

የአውሮፓ ህብረት የሶሪያን መንግሥት በሚወጉት አማፅያን ላይ ጥሎት የነበረውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ለማንሳት የወሰነው በዚሁ በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ነበር ። የህብረቱ አባል ሃገራት በዓመቱ በርካታ የሶሪያ ስደተኞችን ተቀብለዋል ጀርመንም ቃል በገባችው መሠረት ለሶሪያውያን ስደተኞችን አስጠግታለች ። በቀጣዩ ሰኔ ጀርመንና ስድስት የማዕከላዊ አውሮፓ ሃገራትን ያጥለቀለቀው ጎርፍ 19 ሰዎች ገድሎ በቢሊዮኖች ዩሮ የሚቆጠር የኤኮኖሚ ጥፋት አስከትሏል ።

ከዓመቱ አበይት ክንውኖችው በጀርመን ትልቁን ቦታ ከሚይዙት ውስጥ አንዱ የጀርመን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫና የአዲስ መንግሥት ምስረታ ሂደት ናቸው ። በመስከረም ወር የተካሄደው ይኽው ምርጫ በእህትማማቾቹ የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረትና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲዎች አሸናፊነት ነበር የተጠናቀቀው ። ሆኖም ፓርቲዎቹ ያገኙት ድምፅ መንግሥት ለመመስረት የሚያበቃቸው ባለመሆኑ ተጣማሪ ፍለጋው ቀጥሎ በመጨረሻም በምርጫው ሁለተኛ ደረጃ ካገኘው ከሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ SPD ጋር ለ3 ወራት ያህል ተደራድረው ታላቁ ጥምር መንግሥት ዛሬ በሚያበቃው በታህሳስ ወር ተመስርቷል ። የመስከረሙ የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች አሸናፊ የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲ መሪ አንጌላ ሜርክል ታህሳስ 8 2006 ቃለ መሃላ በመፈፀም የመራሄ መንግሥትነቱን መንበር ለ3 ተኛ የስልጣን ዘመን በይፋ ተረክበዋል ።

Demonstration und Proteste in Kiew 26.12.2013 Dmytro Kolchynsky

የዩክሬን ተቃውሞ

በአዲሱ የጀርመን ትልቁ ተጣማሪ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመጀመሪያዋ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር እንዲሁም ዝርያቸው የቱርክ የሆነየመጀመሪያዋ ሚኒስትርም ተሾመዋል ። በአዲሱ የጀርመን ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ አፍሪቃዊ የሆኑ የመጀመሪያው ትውልድ ሴኔጋላዊ የህዝብ እንደራሴም ገብተዋል ።

በቀጣዩ ወር በጥቅምት ከ350 በላይ በአብዛኛው ኤርትራውያን መሆናቸው የተነገረ ስደተኞች አውሮፓ ደጃፍ ደርሰው የውሃ ሲሳይ ሆኑ ። ላሜፔዱዛ አቅራቢያ ከደረሰው ከዚሁ አደጋ 155 ሰስደተኞች ተርፈዋል ። የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ሰሚና ተመልካች አጥተው የሞቱት ስደተኞች ጉዳይ የአውሮፓ ህብረትን በተለይም ኢጣልያን ለብዙ ወቀሳ ዳርጓል ። የአውሮፓ የውጭ ፖሊሲ አማካሪዎች ማዕከል ሃላፊ ዶክተር ሚሪያም ቫን ራይሰን በውቅቱ ችግሩን በጋራ መፍታት እንደሚበጅ ነበር ያሳሰቡት ።

በመጨረሻው በታህሳስ የዓለም ትኩርት ስቦ የቆየው የዩክሬኑ ተቃውሞ ነበር የዩክሬን መንግሥት ከአውሮፓ ህብረት ጋር የንግድና የፖለቲካ ትብብር ውል ላለመፈራረም በመሰወኑ ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎቻቸውን አስቆጥቶ ለብዙ ቀናት የአደባባይ ተቃውሞ አካሂደዋል ።

በሰኔ አገሩን ለቆ ኤኳዶር ጥገኝነት የጠየቀው የአሜሪካን ብሔራዊ የስለላ ድርጅት ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖውደን በነሐሴ ሩስያ ከገባ በኋላ በጥቅምት መውጣት ከወጡት በርካታ ሚስጥሮች ውስጥ የጀርመን መራሄ መንግሥት የአንጌላ ሜርክል ስልክ የመጠለፉ ዜና ነበር ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ኦባም ባስተናገዱበት ዓመት በእጅ ስልክ የሚያደርጉት ንግግር ሳይቀር በሃገራቸው የቅርብ ወዳጅ በዩናይትድ ስቴትስ መጠለፉ ታላቅ ቅሬታና ቁጣ ነበር ያስከተለው

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ