የአውሮጳ ፖርላማ ልዑካን የኢትዮጵያ ጉብኝት | ኢትዮጵያ | DW | 07.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአውሮጳ ፖርላማ ልዑካን የኢትዮጵያ ጉብኝት

የአውሮጳ የሶሻሊስቶችና ዴሞክራቶች አባላት ቡድን ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተነጋግሮ ነበር ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:10 ደቂቃ

የአውሮጳ ፖርላማ ልዑካንበአውሮጳ ፓርላማ የሶሻሊስቶችና ዴሞክራቶች አባላት ቡድን ያዘጋጀው የአፍሪቃ ሳምንት መርሃ ግብር ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ብራሰልስ ውስጥ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተካሄደ ነው። ይኽው ልዩ መርሃ ግብር ፣ ግጭቶችን በማስወገድ በሴቶችና በህጻናት መብቶች በትምህርትና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ዝግጅቶችና ውይይቶች ተካሂደውበታል ። የዚህ መርሃ ግብር አዘጋጅ የአውሮጳ የሶሻሊስቶችና ዴሞክራቶች አባላት ቡድን ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተነጋግሮ ነበር ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ስለ መርሃ ግብሩና ቡድኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ስላካሄደው ውይት ይዘት የቡድኑን ፕሬዝዳንት አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic