የአውሮጳ ኅብረት ሶሪያና መካከለኛው ምሥራቅ  | ዓለም | DW | 17.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአውሮጳ ኅብረት ሶሪያና መካከለኛው ምሥራቅ 

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ የተወያዩት የአውሮጳ ኅብረትን ጨምሮ 70 የሚደርሱ ሀገራት ዲፕሎማቶች ፓሪስ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ እስራኤል እና ፍልስጤማውያን ቀጥተኛ የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ ጥሪ ባቀረቡ ማግስት እንዲሁም የሶሪያ የሰላም ንግግር በካዛክስታን ዋና ከተማ አስታና ከመካሄዱ ከአንድ ሳምንት አስቀድሞ ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

የአውሮጳ ኅብረት ሶሪያ እና መካከለኛው ምሥራቅ 

የአውሮጳ ኅብረት በጦርነት ለተመሰቃቀለችው ሶሪያ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚሻ ጉባኤ በመጪው ሚያዚያ ለማካሄድ ማቀዱን አስታወቀ ። የኅብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራሰልስ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የኅብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ እንደተናገሩት ጉባኤው ከዚህ ቀደም በሶሪያ ሰብዓዊው ይዞታ እንዲሻሻል ቃል የተገባው እርዳታ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በቅርብ ለመፈተሽ እንደሚረዳም አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በሶሪያ እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት ላይ የተወያዩት የአውሮጳ ኅብረትን ጨምሮ 70 የሚደርሱ ሀገራት ዲፕሎማቶች ፓሪስ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ እስራኤል እና ፍልስጤማውያን ቀጥተኛ የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ ጥሪ ባቀረቡ ማግስት እንዲሁም የሶሪያ የሰላም ንግግር በካዛክስታን ዋና ከተማ አስታና ከመካሄዱ ከአንድ ሳምንት አስቀድሞ ነው።  የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ አለው ።


ገበያው ንጉሴ


ኂሩት መለሰ 
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic