1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሕብረትና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባዔ በማልታ

ረቡዕ፣ ኅዳር 1 2008

የአውሮጳ ሕብረትና የአፍሪካ መሪዎች ዛሬና ነገ በማልታ ዋና ከተማ ቫሌታ ላይ በተለይ በስደተኖች ጉዳይ ለመምከር ጉባኤ ተቀምጠዋል።

https://p.dw.com/p/1H43J
Malta EU-Afrika-Gipfel in Valletta
ምስል Getty Images/B. Pruchnie

የአውሮጳ ሕብረትና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባዔ በማልታ

የአውሮጳ ኮሚሽን ከአፍሪቃ የሚመጡትን ስደተኞች ለመግታትና ለስደት የሚያበቁ ችግሮችን ለመፍታት የሚውል 1.8 ቢሊዮን ዩሮ መመደቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ ጉባዔው በእቅዱና አፈጻጸሙ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ፣ የልማት ርዳታውም ሆነ የተነደፈው ስልት፣ የችግሩን መሰረት የሚነካ አይደለም እየተባለ ነው። በተጨማሪም ስደተኖቹ በአውሮጳ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ህይወት ላይ ያሳደሩት ጫና ተጋኖዋል የሚል ክርክርም ይሰማል። የዛሬው ከኢኮኖሚው ዓለም ዝግጅት፣ የቫሌታውን ጉባኤ ሂደትና ውጤት እንዲሁም ስደተኖች በተለይ በአውሮጳ ኢኮኖሚ ላይ የሚያስድሩትን ተጽኖ ይመረምራል።

ገበያዉ ንጉሴ

አርያም ተክሌ