የአውሮጳ ህብረት እርዳታ ለአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብሮች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮጳ ህብረት እርዳታ ለአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብሮች

ውሳኔው በተለይ ከአውሮጳ ህብረት ውጭ በአስቸኳይ ሁኔታ ላይ የሚገኙትን እና የትምሕርት እድል የተነፈጋቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናትን ለመርዳት የሚያስችል ነው ተብሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00

የአውሮጳ ህብረት እና የትምሕርት መ/ግብሮች

የአውሮጳ ሕብረት ግጭት እና የፖለቲካ ቀውስ ባሉባቸው አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብሮችን ለማጠናከር እና ለማስፋት ማቀዱን አስታወቀ። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ባለፈው ዓርብ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ከመጪው የጎርጎሮሳዊው 2019 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ከሰብዓዊ እርዳታ ጠቅላላ በጀቱ 10 በመቶው ለአስቸኳይ ጊዜ ትምሕርት መርሃ ግብር እንዲውል ተወስኗል። ውሳኔው በተለይ ከአውሮጳ ሕብረት ውጭ በአስቸኳይ ሁኔታ ላይ የሚገኙትን እና የትምሕርት ዕድል የተነፈጋቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናትን ለመርዳት የሚያስችል ነው ተብሏል። 

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic