የአውሮጳ ህብረት ርዳታ ለኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 26.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአውሮጳ ህብረት ርዳታ ለኢትዮጵያ

የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያ ወደ 240 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋ የልማት ርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። ይህንኑ ርዳታ የሚመለከተው ስምምነት ትናንት በኢትዮጵያ መንግሥት እና ለጉብኝት አዲስ አበባ በገባው የአውሮጳ ህብረት የልዑካን ቡድን መሪ አንድሪስ ፒባልግስ መካከል ተፈርሞዋል።

EU Development commissioner Andris Piebalgs speaks during a press conference on the new initiative to fight against any kind of discrimination in developing countries at the EU headquarters in Brussels on June 1, 2012. AFP PHOTO / JOHN THYS (Photo credit should read JOHN THYS/AFP/GettyImages) Erstellt am: 01 Jun 2012

አንድሪስ ፒባልግስ

በኢትዮጵያ በልማቱ ዘርፍ በሚንቀሳቀሱ ፕሮዤዎች ላይ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋ በቅርብ የሚሰራው የአውሮጳ ህብረት በሀገሪቱ በልማቱ አኳያ እስከዛሬ የታየው ውጤት አበረታቺ መሆኑን የህብረቱ የልማት ኮሚሽን ቃል አቀባይ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል።

የአውሮጳ ህብረት አሁን ለኢትዮጵያ ዝግጁ ያደረገው ወደ 240 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋው የልማት ርዳታ በከፊል ለሕዝቡ መቅረብ የሚገባውን፣ ማለትም፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣

የጤና ጥበቃ እና የንፁሕ ውኃ አቅርቦትን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶችን የማሟላቱን ስራ እንዲያስችል እና ሴቶች ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ፣ እንዲሁም፣ እየተደጋገመ የሚከሰተው ድርቅ የሚያስከትለውን መዘዝ ለመቋቋም የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትን ለማገዝም ጭምር የታሰበ ነው። የአውሮጳ ህብረት የልማት ኮሚሽን ቃል አቀባይ አሌግዛንድር ፖላክ እንዳስታወቁት፣ ህብረቱ ይህን ርዳታ በአሁኑ ጊዜ ለኢትዮጵያ የሰጠው በዚያ በልማቱ ዘርፍ በተሰራው ስራ በመበረታታቱ ነው።

Autor: Rainer Kwiotek /Zeitenspiegel Menschen für Menschen; Hilfsorganisation; Äthiopien; Afrika; Wasser; Quelle erstellt: 2005, Erer, Äthiopien


« ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋ በተለያዩ ዘርፎች የጀመረው ትብብር ጥሩ ውጤት እያስገኘ ነው። የአንድ ሀገር መንግሥት እና ሲቭሊ ማህበረሰብ ፈታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋሙ ረገድ ውጤታማ እንዲሆኑ ያስቻለ ርዳታ ሊቀጥል ይገባል ብለን ነው የምናስበው። ምክንያቱም ሌሎች ፈታኝ ሁኔታዎ ገና በመኖራቸው። ከነዚህም አንዱ ተደጋግሞ የሚከሰተው ድርቅ ነው። እና የተገኘውን መልካም ውጤት መሠረት በማድረግ ከአጋሮቻችን፣ ከመንግሥት እና ከሲቭል ማህበረሰብ ጋ ባንድነት በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ባተኮሩ ፕሮዤዎች ላይ መስራታችንን ለመቀጠል ወስነናል። »
አሌግዛንድር ፖላክ እንዳስረዱት፣ ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋ ባደረገው የልማት ትብብር ሀገሪቱ ድህነትን ለመቀነሱ፣ የኤኮኖሚ ዕድገትን ለማሳደጉ፣ በወሊድ ጊዜ የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር ለመቀነሱ እና ሕዝቧ ንፁሕ የመጠጥ ውኃ የሚያገኘበትን ሁኔታ ለማሻሻል ያነቃቃቻቸው ጥረቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ህብረቱ ድርሻ አበርክቶዋል። ህብረቱ ከሚደግፋቸው ፕሮዤዎች መካከል በሕፃናት መደዳ የሚታየውን የበቂ ምግብ እጦት ወይም ያልተመጣጠነ አመጋገብ የሚያስከትለውን ችግር የመታገሉ ጥረትም ይጠቀሳል። ህብረቱ ቀጣይ ርዳታ ለመስጠት የሚወስነው የተለያዩት ፕሮዤዎችን ውጤታማነት እያየ መሆኑንም ፖላክ አክለው አስረድተዋል።
ይሁንና፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይረገጣል፣ የፕሬስ ነፃነት አይከበርም በሚል በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ወቀሳ የሚሰነዝሩት የተቃዋሚ ወገኖች እና የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች የህብረቱ ርዳታ አሰጣጥ ይህንን ችላ ብሎዋል ይላሉ፣ አሌግዛነድር ፖላክ ግን ህብረቱ በዚሁ ረገድም ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት።
« ልማትን ከሰብዓዊ መብት ነጥለን ልናይ አንቸልም። በሁሉም ሀገራት፣ በኢትዮጵያ ጭምር ለምሳሌ ከመንግሥት ጋ ስለሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ጭምር የምናነሳበበት የፖለቲካ ውይይት አለን። የሲቭል ማህበረሰባትን የምናጠናክርበት ፕሮዤ አለ፣ የአውሮጳ ህብረት ሚና ሁሉንም ወገኖች መደገፍ እና ኢትዮጵያ የምዕተ ዓመቱን ግብ እንድታሟላ መርዳት ሲሆን፣ የሰብዓዊ መብት እና የፕሬስ ነፃነት መከበርም በዚሁ ውስጥ ይጠቃለላል።»

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic