የአውሮጳ ህብረት፡ ሞሳድ እና በሀማስ ባለስልጣን ግድያ የቀጠለው ክርክር | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአውሮጳ ህብረት፡ ሞሳድ እና በሀማስ ባለስልጣን ግድያ የቀጠለው ክርክር

የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች አንድ ከፍተኛ የሀማስ ባለስልጣን ከአንድ ወር በፊት በዱባይ የተገደሉበትን እና ገዳዮቹ ለዚሁ ተግባራቸው ማካሄጃ በተጭበረበሩ የአውሮጳ ህብረት ፓስፖርቶች የተጠቀሙበትን ድርጊት አወገዙ።

default

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን

በዚሁ ግድያ ዱባይ እስራኤልን ተጠያቂ ስትል ወቀሳ አሰምታለች። ይሁንና፡ በኢራን አቶም ፖሊሲ፡ በሄይቲ፡ በኒዠርና በዩክሬይን ጉዳዮችም ላይ ጭምር የመከሩት ግን ትልቁን ትኩረታቸውን በሀማስ ባለስልጣን ግድያ ላይ ያሳረፉት አውሮጳውያኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ እስራኤልን ለግድያው በቀጥታ ተጠያቂ ከማድረግ ተቆጥበዋል።

ክርስቶፈር ሀስልባኽ/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ