የአዉሮጻ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጓድ ለቻድ | አፍሪቃ | DW | 28.01.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአዉሮጻ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጓድ ለቻድ

የአዉሮጻዉ ህብረት በቻድ እና በማዕከላዊ አፍሪቃ የሰላም አስከባሪ ሃይል ለማሰማራት የሚያስችለዉን ዉሳኔ ዛሪ አጸደቀ። የህብረቱ ሜኒስትሮች ዛሪ ባጸደቁት ዉሳኔ መሰረት 3700 ያህል የህብረቱን ሰራዊት ወደ ቻድ ማዝመት ይጀምራል። የአዉሮጻ ህብረት ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ የህብረቱ ሰላም አስከባሪ ሃይል ወደ ሁለቱ አገራት የሚያዘምተዉ የዳርፉርን ስደተኞች ከአደጋ ለመጠበቅ ነዉ።

የፈረንሳዩ የዉጭ ጉዳይ ሜኒስትር ቤርናድ ካሁነር በብረስሱ ስብሰባ

የፈረንሳዩ የዉጭ ጉዳይ ሜኒስትር ቤርናድ ካሁነር በብረስሱ ስብሰባ

ከአራት ወር ድርድር በኻላ የአዉሮጻዉ ህብረት ዛሪ ታሪክ በቁጥሩ ከፍተኛ የሆነዉን የሰላም አስከባሪ ጓድ ወደ ቻድ እና መካከለኛዉ አፍሪቃ ለመላክ የዉሳኔ ሃሳቡን አጽድቆአል። ሃሳቡን ለማጽደቅ ዘሪ ሰኞ የ 27 ቱ የአዉሮጻዉ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በብራስልሱ ጽህፈት ቤታቸዉ የተቀመጡበት ይህ ወሳኝ ስብሰባ በእንግሊዘኛ ምጽሃረ ቃሉ ኦይፎር EUFOR የተሰኘዉን ከተለያዩ አገራት የመጡ የህብረቱ የሰላም አስከባሪ ጓዶች ወደ ቻድ ለማዝመት የዉሳኔዉን ፊርማ ለማጽደቅ ነበር። 3700 ያህል ወታደሮች ከተለያዩ 14 አዉሮጻ አገሮች የተሰባሰቡት ይህ የሰላም አስከባሪ ጓድ በመጭዉ የካቲት ወር መጀመርያ ግዳጁን እንደሚጀምር ታዉቋል። እንደ ብዙሃን መገናኛዎች መግለጫ በተለይ ከኢርላንድ የመጣዉ የሰላም አስከባሪ ቡድን የዳርፉሩን ወጥረት በመሸሽ ወደ ቻድ የገባዉን ስደተኛ ከለላ እንደሚሰጥ ታዉቋል። ይህ አሁን በየካቲት ወር መጀመርያ ወደ ቻድ እንደሚዘምት የተነገረዉ የአዉሮጻ የሰላም አስከባሪ ጓድ በተለያዩ ምክንያቶች ማለት ከቡድኑ በጎደሉ ወታደሮች እና ለግዳጁ የተለያዩ ቁሳቁሶች ባለመሟላቱ ወደ ቻድ የሚዘምትበት ግዜ እንደተጓተተ ይታወቃል።
በአርላንዱ በጀነራል ፓት ናሽ 3700 የአዉሮጻዉ ህብረት ጠንካራ ጦር እንደሚመራም ዛሪ በብረስልስ የመከረዉ ስብሰባ ይጠቁማል። በጥቅምት ወር ላይ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት 300 ያህል የፖሊስ ሰራዊቶችን በዳርፉር ለሚገኙ ተፈናቃዩችን እንዲቆጣጠር መላኩ የሚታወስ ነዉ።

ከዳርፉር የተፈናቀሉ 234,000 ያህል ስደተኞች ከምስራቃዊ ቻድ 178,000 ያህል ተፈናቃዮች ከመካከለኛዉ አፍሪቃ 43,000 ተፈናቃዮች በአካባቢዉ ላይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ ተጠቁሞዋል። ኦይፎር የተሰኘዉ የህብረቱ ጥምር ጦር በአደጋ ላይ የሚገኙ የሲቢል ነዋሪዎችን ከሽምቅ ተዋጊዎች እንደሚጠብቅ እና ለተፈናቀለዉ ዜጋ ሰባዊ እርዳታዉን እንደሚለግስ ታዉቋል። ጦሩ የሚያደርገዉ ልገሳ 120 ሚሊዮን ይሮ ወይም 176 ሚሊዮን ዶላር ወጭ እንዳለዉ ከወዲሁ ሲገመት የጦር ሰራዊት ባለ ስልጣናት ተጠሪዎች ግን በበኩላቸዉ ወጭዉ ምናልባትም የተጠቀሰዉን አስር እጥፍ እንደሚሆን ገምተዋል።