የአዉሮጳ ፊልም ፊስቲቫል በአዲስ አበባ | ባህል | DW | 13.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የአዉሮጳ ፊልም ፊስቲቫል በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ በሚገኙ አራት የአዉሮጳ አገራት የባህል ተቋማት ዉስጥ፤ ግንቦት 26 የጀመረዉ፤የአዉሮጳ የፊልም ፊስቲቫል፤ እስከ ፊታችን ሰኞ ሰኔ 10 ድረስ ይቀጥላል። በዚህ ፊስቲቫል የተለያዩ የአዉሮጳ ሀገር ፊልሞች ከመታየታቸዉም በላይ፤ የተለያዩ አዉደ ጥናቶችም በመደረግ ላይ ናቸዉ።

ይህ ፊስቲቫል በተለይ በጣልያን የባህል ማዕከል በኩል የተዘጋጀ መሆኑን የገለጹልን፤ በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የጣልያን የባህል ተቋም ዋና ተጠሪ ጣልያናዊዉ ዶክተር ሩጌራ  እንደሚሉት በየዓመቱ የአዉሮጳን ባህል የሚያንጸባርቅ የፊልም ፊስቲቫል ይዘጋጃል። የማህበረሰብ ቋንቋን ባህልን፤ ለማስተዋወቅ፤ ፊልም እጅግ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል ያሉን፤ በኢትዮጵያ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ምክትል ፕሪዚደንት አቶ ደሳለኝ ሃይሉ፤ አቶ ሰለሞን በቀለ ወያ የለቱ መሰናዶ እንግዶቻችን ናቸዉ። መዲና አዲስ አበባ አስራ ሰባት የአዉሮጳ ሃገራትን ያሳተፈ የፊልም ፊስቲቫል እያካሄደች ነዉ ። ይህ ግንቦት ሃያ ስድስት የጀመረዉ የፊልም ፊስቲቫል በአዲስ አበባ በሚገኙ አራት የአዉሮጳ ሀገር የባህል ተቋማት፤ የተለያዩ አዉደ ጥናቶች የሚካሁዱበት እንደሆነም ተነግሮአል።

የጀርመኑ የጎተ የባህል ተቋም፤ የጣልያን የባህል ማዕከል፤ የፈረንሳዪ አልያንስ ፍራንሴስ እና የብሪታንያዉ ብሪቲሽ ካዉንስል በዉጭ ሀገራት የሚገኑ የአዉሮጳ ህብረት የባህል ተቋማት መሆናቸዉን የገለጹት የጣልያን የባህል ማዕከል አስተዳዳሪ ዶክተር ሩጌራ፤ በጋራ የተለያዩ ዝግጅቶችን እንደሚያዘጋጁ እና  ከዚህ መካከል ፊልም ፊስቲቫል እንደሆነም ተናግረዋል።

Straße in Addis Abeba DW-Tage am Goethe Institut Addis Abeba, Äthiopien, alle Fotos: Reategui Die Themen: Sprache, Radio und Sprache, Sprachpolitik in Afrika, Die DW in Äthiopien, Vorstellung des Deutschkurses in Amharisch, Koproduktion mit Radio Ethiopia zum Thema Schuldenerlass, zweiwöchiger Ausbildungskurs des DWFZ für Radiojournalisten und -techniker

 

«በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በፊልም ሥራ ረገድ ያለዉ ሁኔታ አስደናቂ እየሆነ ነዉ። የፊልም ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ እያደገ ነዉ ማለት እችላለሁ። ያም ሆኖ ግን አሁንም ለፊልም ሥራ የሚሆን ቴክኒክ ከፍተኛ እጥረት አለ።  የአገሪዉ ነዋሪም በሀገር ዉስጥ የተሰራ ፊልምን የማየት እጅግ ፍቅር አለዉ። በዚህም ምክንያት የአዉሮጳ ፊልሞች በሀገር ዉስጥ የፊልም አዳራሽ የመታየት ዕድላቸዉ እየመነመነ ሄድዋል። የዚህ ፊስቲቫል አንዱ ዓለማም አንዱ ታድያ የአዉሮጳ ፊልምን ማየት ለሚፈልግ ማህበረሰብ እድል መፍጠር ነዉ። እናም እጅግ ብዙ ተመልካቾችን አግኝተናል»

የኢትዮጵያ የፊልም ስራ እድገት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ የሚነገርላቸዉ፤ የአስቴር ፊልም እና ሌሎች ወደ ሃያ የዘጋቢ ፊልሞች  እንደሰሩ የሚታወቁት አቶ ሰለሞን በቀለ ወያ፤ በአዲስ አበባዉ የአዉሮጳ የፊልም ፊስቲቫል፤ የአዉሮጳ ህብረት ሀገራት ባህላቸዉን አኗኗራቸዉን በፊልም ከማስተዋወቅ ባሻገር የፊልም ስራ ጥበባቸዉንም ለኢትዮጵያዉያኑ እንዲያሳዩ ጠይቀዉ ተሳክቶላቸዋል፤ የማይታይ ብክለት በሚል ርዕስ በአዉሮጳ ህብረት ድጎማ በኢትዮጵያዉያን የፊልም ስራ አዋቂዎች የተሳራዉ ፊልም ላይ ዋና  ተዋናይ የሆኑት የኢትዮጵያ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ምክትል ፕሪዚደንት አቶ ደሳለኝ ሃይሉ፤ ፊልም ፊስቲቫሉ በኢትዮጵያ እና በአዉሮጳ ያለዉን ባህል ለመለዋወጥም ሆነ ለወጣቱ የፊልም ስራ ባለሞያ ጠቀሜታ አለዉ ባይ ናቸዉ።  ሌላዉ ይላሉ የኢትዮጵያ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ምክትል ፕሪዚደንት አቶ ደሳለኝ በመቀጠል እንደ አዉሮጵያዉያን ሁሉ እኛም በተለያዩ አገራት ባህላችን የምናስተዋዉቅበት ማዕከልን መክፈት መቻል አለብን።

ፊልም  ምስል ብቻ  ሀገርን ባህልን ማንነትን እና ፍላጎትን በቀላል ማስተዋወቅ የሚችል፤ ታላቅ መሳርያ በመሆኑ በሀገራችን ለፊልም ሥራ እድገት የሚደረገዉ ድጋፍ መጠንከር እና መበረታታት አለበት ያሉንን በለቱ ቅንብራችን ቃለ ምልልስ የሰጡን ተሳታፊዎች በሙሉ በዶቼ ቬለ ሥም እናመሰግናለን።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ 

Audios and videos on the topic