የአዉሮጳ እና አፍሪቃ ግንኙነት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 02.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ እና አፍሪቃ ግንኙነት

የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ግንኙነት ረዥም ዘመን አስቆጥሯል።  አፍሪቃ በአዉሮጳ ሃገራት ቅኝ ከመገዛት ነፃ ከወጣ በኋላ የሁለቱ አህጉራት ግንኙነት የቅኝ ገዢ እና ተገዢ አይነት ሆኖ ቆይቷል። በአብዛኛዉም የእርዳታ ሰጪና ተቀባይነት ትስስሩ ይጎላል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:01

ከቅኝ ገዢ እና ተገዢነት ግንኙነት እየተለወጠ ነዉ፤

ከቀዝቃዛዉ ጦርነት በኋላ የምሥራቁ ጎራ ሲፈራርስ፤ አፍሪቃ ከአዉሮጳ ጋር ለሚኖራት ትስስር ዴሞክራሲ ማስፈን፤ የሰብአዊ መብቶችን ማክበር፣ እንዲሁም የነጻ ገበያ መርህ እና የመሳሰሉት ፅንሰ ሃሳቦች ከምዕራቡ ዓለም ጋር ለሚደረጉ ግንኙነቶች እንደመሠረት ይወሰዳሉ በሚል እስካሁን ይነገራል። በመልካም አስተዳደር እና ተያያዥ ምክንያቶች ሰበብ ከአፍሪቃ ተሰዳጆች መበርከታቸዉ፣ እንዲሁም የሽብር እንቅስቃሴ ያሰጋዉ አዉሮጳ ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት በቅኝ ገዢነት በቅርብ ከሚያዉቃት አፍሪቃ ጋር የተለየ ጉድኝት እንደሚያሻዉ በማመላከት አዲስ ትብብር በሁለቱ አህጉሮች መካከል መሥርቷል። የትራምፕ አስተዳደር ያፈነገጠ አካሄድ፣ የቻይና በአፍሪቃ እንደልብ መንቀሳቀስ፤ የብሪታኒያ ከኅብረቱ መዉጣት ለአዉሮጳ በቅርብ ርቀት ከምትገኘዉ ከአፍሪቃ የተሻለ ተጓዳኝ እንደሌለዉ ያመላከተ መስሏል። በዘንድሮዉ አዲስ ዓመትስ የሁለቱ ግንኙነት እንዴት ይቀጥል ይሆን? የዕለቱ አዉሮጳ እና ጀርመን መሰናዶ የአፍሪቃ እና አዉሮጳን ግንኙነት ይቃኛል። 

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic