የአዉሮጳ ኅብረት ወንጀልን በገንዘብ የመርዳት ቁጥጥር መመርያ  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ኅብረት ወንጀልን በገንዘብ የመርዳት ቁጥጥር መመርያ 

መቀመጫዉን ብራስልስ ያደደረገዉ የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ግንቦት 12 ቀን 2007 ዓ.ም ገንዘብ ማሻሽን የሚቃወምና በገንዘብ ሽብርን መደገፍን የሚጻረር መመርያን ማፅደቁ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:50

አዉሮጳ ኅብረት

በኅብረቱ  መመርያ አንቀፅ 9 ዉስጥ እንደተጠቀሰዉ ገንዘብን ማሽሽና ሽብርን በገንዘብ መደገፍን የሚቀጣ የእቅድ እጥረት ያላባቸዉ ታዳጊ ሃገራት በአዉሮጳ ኅብረት የገንዘብ አጠቃቀም ስርዓት ስጋት መደቀናቸዉ ተጠቅሶአል። ስጋት ደቅነዋል ከተባሉት ታዳጊ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ከሁለት ሳምንት በፊት የኅብረቱ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል። አንድን አገር በገንዘብ ማሽሽና ሽብር በገንዘብ መደገፍን የሚቀጣ የእቅድ እጥረት አላቸዉ ለማለት መስፈርቱ ምንድ ናቸዉ?

በአዉሮጳ ኅብረት የሕግ ጉዳይ ክፍል ቃል አቀባይ አቀባይ ክርስትያን ቪጋንድ ያስረዳሉ፣ « ሃገራት በኅብረቱ ላይ ስጋት ያሳድራሉ የሚያስብል መሰፈርት በጣም ቴክኒካዊ ነዉ። ገንዘብን ማሽሽና ሽብርን በገንዘብ መደገፍን የሚቀጣ የእቅድ እጥረት አላቸዉ የሚያስብል መስፈርት ገንዘብ የሚያሸሹት ወይም ሽብርን በገንዘብ የሚደግፉትን በወንጀል የምቀጣ እቅድ እጥረት ስላላቸዉ ነዉ። ለምሳሌ ነገሮችን መዝግቦ  በትክክል አለመያዝ፣ በጥርጣሪ የሚታዩት የገንዘብ ዝዉውር ላይ ዘገባ አለማቅረብና ተያያዥ ችግሮች ሲከሰቱ  መፍቴ አለመስጠት ይገኙባቸዋል።»

ገንዘብ ማዘዋወርና ሽብርን በገንዘብ መርዳት በምስራቅና በአፍርቃ ቀንድ እየተንሰራፋ  የመጣ ሃይለኛ የወንጀል እንቅስቃሴ መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ። «ሴንቴር ኦን ግሎባል ካዉንቴር ቴሬሪዝም ኮኦፕሬሼን» እንደ ጎርጎረስያዊያኑ በ2013 ዓ,ም ባወጣዉ ዘገባ  ኢትዮጵያ ገንዘብ ማሻሽንና በገንዘብ ሽብርን መደገፍ የሚያባብስ አስጊ ወንጀል ሊፈፀምባት የሚችል አገር ሲል ጠቅሰዋል። አስጊ ወንጀሎች የሚላቸዉም ሙስና በመንሰራፋቱ፣ ግብር ማጭበርበር፣ ደካማ ድንበር ጥበቃ መኖሩና ሕገወጥ የሰዉ፣ የመሳርያና የአደንዛዥ ዕፅ ዝዉውር የሚታይባት ሃገር መሆኗን ያትታል።

ኢትዮጵያን ገንዘብን ማሽሽና ሽብርን በገንዘብ መደገፍን የሚቀጣ የእቅድ እጥረት አላት ያሉበትን ምክንያት የአዉሮጳ ሕብረት የሕግ ጉዳይ ክፍል ቃል አቀባይ  ቪጋንድ ለዶይቼ ቬሌ ይህን ተናግረዋል፣ «በኢትዮጵያ ያለዉ ጉዳይ በምሳሌ ለመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ ገንዘብ የሚያሸሹና በገንዘብ ሽብርን የሚረዱ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ያሳየችሁ መነሳሳት በጣም ዝቅተኛ ነዉ። ይሄም ለምሳሌ ግዴታ ያለባቸዉ ተቋማት ቁጥጥር ያለማድረግ፣ ከዓለም አቀፉ የስለላ ድርጅት የሚመጡትን መረጃዎች አለመጠቀም፣ ወንጀለኞችን አለመቅጣትና በወንጀል እንቅስቃሴዎች የሚመጡትን ንብረቶች አለመዉረስ ይገኙበታል።»


የአዉሮጳ ኅብረት መረጃ እንደምያመለክተዉ ኢትዮጵያ ችግሮቹን ለመፍታት ከፍተኛ የፖለትካ ተነሳሽነት እንዳላት ለኅብረቱ መግለፅዋም ተመልክቶአል።  ይህን ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንግስትም ፅኑ የፖለቲካ መነሳሳት እንዳለዉ ለኅብረቱ በጽሑፍ ማስገባቱን ከኅብረቱ የተገኘ መረጃ ያሳያል። በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጡን ያደርግነዉ ሙከራ አልተሳካም።  

መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic