የአዉሮጳ ኅብረትና የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 26.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአዉሮጳ ኅብረትና የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ

የአዉሮጳ ኅብረትና የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ የግብርና ልማት ፕሮጀክት መርጃ የሚሆን የ 3,8 ሚሊዮን ርዳታ ለመለገስ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ተስማሙ።


ርዳታዉ በተለይ ማኅበራዊና አካባቢያዊ ተኮር ለሆነ የግብርና ልማት ማስፋፍያ ፕሮጀክት እንደሚዉል ተገልጾአል። የኢትዮጵያ የግብርና ልማት የመሬት አስተዳደር ኤጀንሲና በግብርና ሚኒስቴር ተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ መምሪያ ለፕሮጀክቶቹ ተግባራዊነት ኃላፊዎች ናቸዉ ተብሎአልም። ፕሮጀክቶቹ ማኅበራዊ ጠቀሜታ ያላቸዉና ለአካባቢያዊ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጡ ተጠያቂነትና ግልፅነት ያላቸዉ እንዲሁም የአካባቢዉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የግብርና ልማቶችን የሚያግዙ እንደሆኑም ተነግሮአል።

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic