የአዉሮጳ ኅብረትና ሩሲያ ጉባኤ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 12 2005ማስታወቂያ
ሁለቱ ወገኖች በአዉሮጳ ኅብረት ሀገሮች እና በሩሲያ መካከል መሠረታዊ በሆነዉ በኃይል አቅርቦት፤ ሞስኮ የሶርያን ቀዉስ አስመልክቶ በያዘችዉ አቋም፤ እንዲሁም በሩሲያ የሰብዓዊ መብት እና የተቃዉሞ ፖለቲካዉ ወገን አያያዝ ላይ ሰፊ ዉይይት አካሂደዋል። ሩሲያ ዜጎቿ ወደሌሎች የአዉሮጳ ሀገሮች ያለ ይለፍ እንዲሸጋገሩ ያቀረበችዉ ጥያቄም ዳግም ያነጋገረ ሲሆን ከ27ቱ የኅብረቱ መንግስታት ጋ ያላት የንግድና መሰል ግንንኙነቶችም ተነስተዋል። ዉይይቱ ሲያበቃ ዛሬ ከቀትር በኋላ የነበረዉን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉን የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ