የአዉሮጳ ሻምፒዮና ሊግ | ስፖርት | DW | 01.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የአዉሮጳ ሻምፒዮና ሊግ

በዘንድሮዉ የአዉሮጳ ሻምፒዮን ሊግ የጀርመን ክለቦች ጎልተዉ መዉጣታቸዉ የሰሞኑ የስፖርት የሞቀ ዜና ነዉ።የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የስፓኙን ባርሴሎና አራት ለዜሮ አባሮ ዛሪ ዳግም እስፓኝ ላይ ሊገጥመዉ በዝግጅት ላይ ነዉ። ሌላኛዉ የጀርመን ክለብ ቦሪሲያ ዶርትሙንድ ሌለኛዉን የስጳኝ ቡድን ሪል ማድሪድን ...

ባለፈዉ ሰሞን የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የስፓኙን ባርሴሎና አራት ለዜሮ አባሮ ዛሪ ዳግም እስፓኝ

በኖርድራይንቬስትፋለን ፌደራል ክፍለ ሀገር ሰሜናዊ ክፍል ፣ በዶርትሙንድ ከተማ የሚገኘው እ ጎ አ ታኅሳስ 19 ቀን 1909 ዓ ም የተመሠረተው ፣ Ballspiel Verein Borussia 09 በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የጀርመን የአንደኛ ምድብ የአግር ኳስ ክለብ፤ ትናንት ማታ ማድሪድ ውስጥ ፣ ከሪያል ማድሪድ ክለብ ጋር የመልስ ግጥሚያ አካሂዶ 2-0 ቢሸነፍም በመጀመሪያው ዙር 4-1 አሸንፎ ስለነበረ ፣ ግንቦት 17 ቀን 2005 ለንደን ዌምብሊ እስታዲዮም ለሚካሄደው የዋንጫ ፍጻሜ ግጥሚያ ማለፉን አረጋገጠ። ዛሬ ማታ ባርትሴሎና ላይ ፤ ባየርን ሙዑንሸን በአጠቃላይ ውጤት አሸንፎ ካለፈ ለፍጻሜ ግጥሚያ የሚወዳደሩት 2 የጀርመን ክለቦች ይሆናሉ ማለት ነው። ይህም ለጀርመን እግር ኳስ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ማለፊያ ዕጣ እንደሚሆን በመነገር ላይ ነው። ዶርትሙንድ ትናንት ማታ ጨዋታው አልቆ ማለፉን እንዳረጋገጠ። ተከላካይ ኔቨን ሱቦቲክ ስለጨዋታው እንዲህ ብሏል።
«አጠቃላዩን ጨዋታ መገምገም ይቻላልና፣ አድልዎ ተፈጽሟል ብሎ ማማረሩ እኛንም እንዴት ብለን እንድንሦረፍ የሚያደርግ ነው እኝም ብንሆን ስሜታውያን መሆናችን ሊዘነጋ አይገባም። ይኼ አድልዎ ተደረገ መባሉ፤ እወነቱን ለመናገር፣ እጅጉን የሚያናድድ ነው።»
አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ በበኩሉ እንዲህ ነበረ ያለው።
«ጨዋታው ማለቁን የሚያበሥረው ፊሽካ ሲነፋ፤ ማመን ነው ያቃተኝ። ባልደረቦቼ፣ በደስታ ሲያለቅሱ አይቼአለሁ። ገሚሱ ተጫዋጮች ጉልበታቸው ዝሎ፤ ደክሞአቸው ሜዳ ላይ እስከመጋደም ነበረ የደረሱት ፤ ፍጹም የማልረሰው ልዩ ትዝታ ነው።» ዶርትሙንድ ትናንት በመለሱ ጨዋታ ሁለት ለዜሮ ቢሸነፍም ለአዉሮጳ ሻንፒዮና የዋንጫ ግጥምያ ማለፉን አረጋግጧል፤ የበርሊኑ ዘጋብያችን ይልማ ሃ/ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ሃ/ሚካኤል

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic