የአዉሮጳ ሻምፒዮና ሊግ | ስፖርት | DW | 25.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የአዉሮጳ ሻምፒዮና ሊግ

በዘንድሮዉ የአዉሮጳ ሻምፒዮን ሊግ የጀርመን ክለቦች ጎልተዉ መዉጣታቸዉ የሰሞኑ የስፖርት የሞቀ ዜና ነዉ።

በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የስፓኙን ባርሴሎና በዜሮ የመሸኘቱ ወሬ ናኝቶ ሳያበቃ ትናንት ማምሻዉን ቦሪሲያ ዶርትሙንድ ሪያል ማድሪድን አራት ለአንድ ወይም ሶስት ለባዶ ማሰናበቱ የጀርመንን የኳስ አፍቃሪዎች ብቻ ሳይሆን የአብኛዉን ወገን ቀልብ ስቧል። አንዳንድ ዘገባዎች በድንቅ አጨዋወታቸዉ የሚያፈዙት የስፓኝ ኮከብ ተጫዋጮች ወደታዋቂነቱ መሰላል አዲስ መዉጣት በጀመሩ የጀርመን ፈጣን አጥቂዎች ጥላ መከለላቸዉን እየገለፁ ነዉ። የአዉሮጳ የሻምፒዮን ሊግም ምናልባት በሁለት የጀርመን ክለቦች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የፍፃሜ ጨዋታዉን ያስተናግዳል የሚሉም አሉ። የጀርመን ክለቦች ጎልቶ መዉጣትና የስፓኞችን መደብዘዝ አስመልክቶ ሳምንታዊ ስፖርት ጥንቅሮችን የሚያቀርብልንን ባልደረባዬ መስፍን መኮንን በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

መስፍን መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ