የአዉሮጳ ሕብረት ጦር በማሊ | አፍሪቃ | DW | 02.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአዉሮጳ ሕብረት ጦር በማሊ

ከሁለት መቶ ከሚበልጡት የአዉሮጳ ሕብረት አሠልጣኞች መካካል ሰማንያዉ የጀርመን ወታደሮች ናቸዉ።

German Defence Minister Thomas de Maiziere (R) meets with members of a German Bundeswehr soldier advisory group, on arrival at the airport in Bamako March 18, 2013. REUTERS/Oliver Lang/Pool (MALI)

የጀርመን መከላከያ ሚንስትር ማሊ ከሠፈሩ የሐገሪቱ ወታደሮች ጋር

  
የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ማሊ ያዘመቱት አሠልጣኝ ሠራዊት ዛሬ የማሊ ወታደሮችን ማሠልጠን ጀምሯል።ከሁለት መቶ ከሚበልጡት የአዉሮጳ ሕብረት አሠልጣኞች መካካል ሰማንያዉ የጀርመን ወታደሮች ናቸዉ።የሥልጠናዉ አላማ የማሊ ጦር ሰሜናዊ ማሊ የሸመቁ የሙስሊም አክራሪ ደፈጣ ተዋጊዎችን የመዉጋት ብቃቱን ማዳበር ነዉ።የሙስሊም እና የቱአሬግ ደፈጣ ተዋጊዎች የፈረንሳይ ጦር እስከዘመተባቸዉ ጊዜ ድረስ አብዛኛዉ የሰሜናዊ ማሊ ግዛት አብዛኛ ግዛቶች ይቆጣጠሩ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረት አሠልጣኖች በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ ከሠወስት ሺሕ በላይ የማሊ የጦር መኮንኖችንና ወታደሮች ለማስተማር አቅደዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic