የአዉሮጳ ሕብረት የስደተኞች መርሕ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 07.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ሕብረት የስደተኞች መርሕ

አንዳድ የመብት ተሟጋቾች ከሰወስት መቶ ሐምሳ በላይ ኤርትራዉያን ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ሲሞክሩ ላፑዱዛ አጠገብ በደረሰዉ የጀልባ አደጋ ሰምጠዉ ለመሞታቸዉ የአዉሮጳ ሕብረትን የስደተኞች መርሕ ተጠያቂ ያደርጋሉ

የላምፔዱዛዉ መዳራሻ የባሕር ላይ አደጋ፥ አሁንም የአዉሮጳ ሕብረት ፖለቲከኞችንና የመብት ተሟጋቾችን እያወዛገበ ነዉ።አንዳድ የመብት ተሟጋቾች ከሰወስት መቶ ሐምሳ በላይ ኤርትራዉያን ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ሲሞክሩ ላፑዱዛ አጠገብ በደረሰዉ የጀልባ አደጋ ሰምጠዉ ለመሞታቸዉ የአዉሮጳ ሕብረትን የስደተኞች መርሕ ተጠያቂ ያደርጋሉ።የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች ለዉጪ ስደተኞች አዲስ መርሕ የሚያጠና ግብር-ሐይል ሰይመዋል።ትናንት ብራስልስ-ቤልጂግ ተሰብስበዉ የነበሩ የስደተኞች መብት ተሟጋቾች፥ ሙሕራንና የምክር ቤት እንደራሴዎች ግን የአዉሮጳ መንግሥታትን በድጋሚ ወቅሰዋል።ገበያዉ ንጉሴ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic