የአዉሮጳ ሕብረት ዉ.ጉ ሚኒስትሮች ስብሰባ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ሕብረት ዉ.ጉ ሚኒስትሮች ስብሰባ

የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት በሉክዘንበርግ ባካሄዱት ስብሰባ የኤቦላ ተሐዋሲ መዛመት ስለሚገታበት ርምጃ ተወያይተዋል።

ከዚህም ሌላ ሚኒስትሮቹ በኢራቅና ሶሪያ የሚንቀሳቀሰዉ ራሱን «እስላማዊ መንግሥት»ብሎ ከሚጠራዉ በምሕጻሩ ISIS ከተሰኘዉ አክራሪ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ጋ በመካሄድ ላይ ስላለዉ ፍልሚያ፤ በሊቢያ ስላለዉ ወቅታዊ ሁኔታ፤ እንዲሁም በዩክሬንና በሌሎችም አካባቢዎች ስለሚታዩ አሳሳቢ የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዉ ዉሳኔዎችም አሳልፈዋል። በተለይም ሚኒስትሮቹ ኤቦላን አስመልክተዉ ባካሄዱት ዉይይት በሽታዉ ያልተጠበቀ ዓለም ዓቀፍ ቀዉስ ማስከተሉን አምነዉ፤ ችግሩን ለመግታትና ለማስወገድም የሁሉም ትብብርና የተቀናጀ አሠራር የሚያስፈልግ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዉታል። የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic