የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔ እና ሒዝቡላሕ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔ እና ሒዝቡላሕ

ሒዝቡባላሕ ግን ፍረጃዉን «የአሜሪካና የፅዮናዉያን ሴራ» በማለት ሲያወግዘዉ፥ የሊባኖስ መንግሥት ደግሞ ለሊባኖስ «ተጨማሪ ችግር ፈጣሪ» በማለት ተቃዉሞታል።የፖለቲካ ተንታኞችም የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔን ገቢራዊነት ይጠራጠራሉ

የአዉሮጳ ሕብረት የሊባኖሱን ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕን በአሸባሪነት መፈረጁን እራሱ ሒዝቡላሕና የሊባኖስ መንግሥት አወገዙት።ሕብረቱ፥ እስራኤል በሐይል የያዘችዉን የሊባኖስ ግዛት ነፃ ለማዉጣት የሚፋለመዉን ቡድን በአሸባሪነት የፈረጀዉ ቡድኑ በሶሪያዉ ጦርነት ጣልቃ ገብቷል፥ እስራኤላዊ ሐገር ጎብኚዎችን አስገድሏል በሚል ነዉ።ሒዝቡባላሕ ግን ፍረጃዉን «የአሜሪካና የፅዮናዉያን ሴራ» በማለት ሲያወግዘዉ፥ የሊባኖስ መንግሥት ደግሞ ለሊባኖስ «ተጨማሪ ችግር ፈጣሪ» በማለት ተቃዉሞታል።የፖለቲካ ተንታኞችም የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔን ገቢራዊነት ይጠራጠራሉ።ሥለ ዉሳኔዉ እና አፀፋዉ የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic