የአዉሮጳ ሕብረት ወታደራዊ ዘመቻ | ዓለም | DW | 19.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአዉሮጳ ሕብረት ወታደራዊ ዘመቻ

የሕብረቱ አባል ሐገራት የዉጪና የመከላከያ ሚንስትሮች ትናንት ባሳለፉት ዉሳኔ መሠረት ጠቅላይ ዕዙን ሮም-ኢጣሊያ ያደረገ ባሕር ሐይል በቅርቡ ይመሠረታል።

የአዉሮጳ ሕብረት ሥደተኞችን በሜድትራኒያን ባሕር በኩል ወደ አዉሮጳ ለማስገባት የሚሞክሩ ሥደተኛ አዘዋዋሪዎችን የሚመታ የባሕር ጦር ሊያዘምት ነዉ።የሕብረቱ አባል ሐገራት የዉጪና የመከላከያ ሚንስትሮች ትናንት ባሳለፉት ዉሳኔ መሠረት ጠቅላይ ዕዙን ሮም-ኢጣሊያ ያደረገ ባሕር ሐይል በቅርቡ ይመሠረታል።ሚንስትሮቹ በነደፉት ዕቅድ መሠረት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤትን ይሁንታ እንዳገኘ ጦሩ እርምጃ ይወስዳል።የመብት ተሟጋችና የስደተኞች ተቆርቋሪዎች ግን የሕብረቱን የሐይል እርምጃ ዕቅድ አጥብቀዉ ተቃዉመዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic