የአዉሮጳ ሕብረት፥ ብሪታንያና ጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ሕብረት፥ ብሪታንያና ጀርመን

ከሁለት ሳምንት በሕዋላ በሚደረገዉ ጉባኤ ካሜሩን ሌሎቹን መሪዎች ከመሰሉ፥ የአዉሮጳን ምጣኔ ሐብት የምትማራዉ፥ለከሰሩት ሐገራት ከፍተኛዉን ብድርና ድጎማ የምትሰጠዉ ጀርመን እንደ

Britain's Prime Minister David Cameron greets German Chancellor Angela Merkel (R) at Downing St in central London on November 7, 2012. Merkel on Wednesday warned Britain not to turn its back on Europe ahead of talks in London with Prime Minister David Cameron aimed at overcoming divisions that threaten to block a European Union budget deal later this month. REUTERS/Olivia Harris (BRITAIN - Tags: POLITICS)

ሜርክልና ካሜሩን

ሐገር፥ ሜርክል እንደ መሪ አዉሮጶችን አግባቢነታቸዉን አስመሰከሩ ማለት ነዉ።

የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልና የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን ትናንት ለንደን ዉስጥ ባደረጉት ዉይይት የአዉሮጳ ሕብረት ሕብረት በጀትን ለመወሰን «አግባቢ» ነጥብ ላይ ድረሰዋል።ሁለቱ መሪዎች ትናንት ማታ እራት ላይ ያደረጉት ዉይይት ካበቃ በሕዋላ ከብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ፅሕፈት ቤት የወጣዉ መግለጫ እንዳመለከተዉ ሕብረቱ በጀቱን በተመለከተ የአበል ሐራት ሕዝብ የሚሰጠዉን አስተያየት መቀበል አለበት በሚለዉ ሐሳብ መሪዎቹ ተስማምተዋል።የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ግን ብሪታንያ በአዉሮጳ ሕብረት በጀት ብቻ ሳይሆን ሥለ ሕብረቱ አጠቃላይ አሰራር ከሌሎቹ አባል ሐገራት ጋር ብዙም አትግባባም።ሜርክልን ለንደን ድረስ ያጓዘዉም ብሪታንያ አቋሟን እንድታለዘብ ለማግባባት ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።


የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች ከሁለት ሳምንት በሕዋላ በሚያደርጉት ጉባኤ ሕብረታቸዉ እ.ጎ.አ.ከ2014 እስከ 2020 ባለዉ ጊዜ የሚያስፈልገዉን በትሪሊዮን የሚቆጠር በጀት ይወስናሉ። የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን ግን ሕብረቱ ወጪዉን መቀነስ አለበት ባይ ናቸዉ።

የጋራዉ ማሕበር በተለይ በዚሕ የምጣኔ ሐብት ድቀት ወቅት ወጪዉን ለመቀነስ ካልፈቀደ ካሜሩን እንደዛቱት የበጀት ረቂቁን ድምፅን በድምፅ በመሻር ሥልጣናቸዉ ዉድቅ ያደርጉታል።የካሜሩን ዛቻ ብሪታንያ ወትሮም የሕብረቱን ሥራ እና አሠራር ከመደገፍ ይልቅ ማንቀፉ ነዉ-የሚቀናት እያሉ ለሚተቿት ወገኖች የተጨማሪ ትችት ምክንያት፥ለሌሎቹ የሥጋት ምንጭ ነዉ የሆነዉ።

ብራስልስ የሚገኘዉ የአዉሮጳ መርሕ ጥናት ማዕከል ባልደረባ ማርኮ ኢንሰርቴ እንደሚሉት ደግሞ የካሜሩን ዛቻ ብሪታንያን ላለማጣት ብዙ የሚታገሉትን ሐይላት ልፋት መና የሚያስቀር አይነት ነዉ።

«እስከ ቀርብ ጊዜ ድረስ አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሕብረት ወዳጆች ብሪታንያ በሕብረቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ሙሉ ተሳታፊ እንድትሆን ለማድረግ አበክረዉ ሲጥሩ ነበር።አሁን ግን ይሕ እንዳልሰራ እያዩት ነዉ»አንጌላ ሜርክልን ትናንት ማታ ከበርሊን ለንደን አድርሶ የመለሰዉም የካሜሩን ዛቻ ነዉ።ሜርክል በቢላ፥ ሹካ፥ ማንኪያዉ ቅጭልቅልታ፥ በብርጭቆ ጠርሙሱ ግጭ-ግጭታ መሐል የእራት ጋባዣቸዉን ሐሳብ ማስቀየር አለማስቀየራቸዉ በዉል አልታወቀም።

ሕብረቱ በተለይ የአዉሮጳ ምጣኔ ሐብት በኪሳራ ቁል ቁል በሚዘቅጥበት ባሁኑ ወቅት ተጨማሪ ወጩዎቹን መቀነስ፥ የሕዝብ አስተያየትንም መቀበል አለበት በሚለዉ ሐሳብ ሁለቱም መሪዎች መስማማታቸዉን ከካሜሩን ፅሕፈት ቤት የወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል።

የካሜሩን ሐሳብ ግን የቀድሞዉ የቤልጂግ ጠቅላይ ሚንስትር ጉይ ፈርሆፍሽታት እንደሚሉት የሕብረቱ ወጪ ወይም በጀት ብቻ አይደለም።ብሪታንያ ሥለ ሕብረቱ ያላት የቆየ፥ መንታ አቋም ነፀብራቅ ነዉ።

«እንደሚመስለኝ ከብሪታንያ ጋር መሠረታዊ ችግር አለ፥ ምክንያቱም የሕብረቱ አካል መሆን ይፈልጋሉ ግን ደግሞ በየትኛዉም የሕብረቱ መርሕ አይሳተፉም።የቡድኑ አባል ሆኖ፥ የቡድኑን ግጥሚያ አለመጫወት አዳጋች ነዉ»

የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ሲበዛ፥ብሪታንያ ከሕብረቱ አባልነት መዉጣት አለበት በሚሉ፥ ሲያንስ ብሪታንያ ለሕብረቱ የምትከፍለዉን መዋጮ መቀነስ አለባት የሚሉ የፓርቲያቸዉን አባላት በግባባቱና የሕብረቱን ደንቦች በማክበሩ መሐል ተቃርጠዋል።ሕብረቱ ዉጪዉን ይቀነስ የማለታቸዉ ምክንም አጣብቂኝ በመግባታቸዉ ነዉ ባዮች ብዙ ናቸዉ።

ARCHIV - Ein Mann nimmt Euro-Geldscheine aus einer Geldbörse (Archivfoto vom 29.11.2001). Mit dem neuen Jahr kommen auf die Bundesbürger zahlreiche Änderungen zu, die sich auch im Geldbeutel bemerkbar machen. Am stärksten schlägt die Erhöhung der Mehrwertsteuer von 16 auf 19 Prozent zu Buch. Für manche Familien gibt es auch Entlastung: Das bisherige Erziehungsgeld wird durch ein Elterngeld ersetzt. Es orientiert sich am bisherigen Einkommen des betreuenden Elternteils. Foto: Frank Kleefeldt dpa +++(c) dpa - Bildfunk+++

ዩሮ

የሕብረቱ የበጀት ጉዳይ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ፋብሪሶ ፍዮሪሊ እንደሚሉት ግን ካሜሩን ያሉትን ማለታቸዉ የዲሞክራሲያዊዉ አሠራር ገፅታ በመሆኑ ሊያስወቅሳቸዉ አይገባም።

«ብሪታንያን በየትኛዉም መንገድ ቢሆን መነጠል የለብንም።በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሑሉም ሐሳቡን መግለፅ አለበት።ጉዳዩ ጥሩ አይደለም ብለዉ ካሰቡ ሃያ ሰባቱ አባል መንግሥታት ድምፅን በድምፅ መሻር ይችላሉ።ይሕ የተለመደ ነዉ።»

ከሁለት ሳምንት በሕዋላ በሚደረገዉ ጉባኤ ካሜሩን ሌሎቹን መሪዎች ከመሰሉ፥ የአዉሮጳን ምጣኔ ሐብት የምትማራዉ፥ለከሰሩት ሐገራት ከፍተኛዉን ብድርና ድጎማ የምትሰጠዉ ጀርመን እንደ ሐገር፥ ሜርክል እንደ መሪ አዉሮጶችን አግባቢነታቸዉን አስመሰከሩ ማለት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic