የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት እና ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 21.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት እና ኢትዮጵያ

ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ለሚመክረዉ ምክር ቤት የቀረበዉ ረቂቅ ዉሳኔ የዚትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በኦሮሚያ መስተዳድር ለተቃዉሞ አደባባይ የወጡ ሰዎችን ገድሏል፤ በሺሕ የሚቆጠሩትን አስሯል፤ የጋዜጠኞችን መብት ሳይቀር ይርግጣል የሚሉ ሐሳቦችን ያካተተ ነዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:33

የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት እና ኢትዮጵያ

የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት እንደራሴዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ይፈፀማል ሥለሚባለዉ የሠብአዊ መብት ጥሠረት በቀረበ የዉሳኔ ሐሳብ ላይ እየተወያዩ ነዉ።ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ዛሬ ለሚመክረዉ ምክር ቤት የቀረበዉ ረቂቅ ዉሳኔ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በኦሮሚያ መስተዳድር ለተቃዉሞ አደባባይ የወጡ ሰዎችን ገድሏል፤ በሺሕ የሚቆጠሩትን አስሯል፤ የጋዜጠኞችን መብት ሳይቀር ይርግጣል የሚሉ ሐሳቦችን ያካተተ ነዉ።የምክር ቤቱ የሶሻሊስት እና የሊቢራል ወይም ለዘብተኛ ፓርቲ እንደራሴዎች ያረቀቁት ሐሳብ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ጋር ያለዉን ግንኙነት ዳግም እንዲያጤን የሚጠይቅ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን ሥለ ረቂቁ ጠይቄዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ

Audios and videos on the topic