የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 14.12.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ

የፖለቲካ ተንታኞችና ታዛቢዎች እንደሚሉት ግን መሪዎቹ ተስፋ ከመስጠታቸዉ ባለፍ ተስማሙበት የተባለዉ አዲስ መርሕ አባል ሐገራትን የገጠመዉን ቀዉስ ለማስወገድ እስካሁን ከተወሰዱት እርምጃዎች ብዙ የሚፈይደዉ ነገር የለም።

default

መሪዎቹ

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የዩሮ ሸርፍ ተጋሪ ሀገሮች የገጠማቸዉ አስከፊ ቀዉስ ገና አለማክተሙን አመለከቱ። የአዉሮጳ ኅብረት ለሁለት ቀናት ያካሄደዉን የዓመት መዝጊያ ጉባኤ ሲያጠቃልል ሜርክል ለዘጋቢዎች እንደገለፁት የዩሮ ተጠቃሚ ሀገሮች የተጋፈጧቸዉ አስቸጋሪ የማስተካከያ ርምጃዎች፤ የሚታየዉ አዝጋሚ እድገትና የሥራ አጡ ቁጥር መጨመሩ ችግሩ እንዳላበቃ አመልካች መሆኑንም ገልፀዋል። ተግባራዊ የተደረጉ ማስተካከያዎች ዉጤትም የሚታይበት ጊዜ ገና መሆኑን ሜርክል ግልፅ አድርገዋል። የኅብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ጆሴ ማኑዌል ባሮሶ በበኩላቸዉ ተሰናባቹ የጎርጎሮሳዊ ዓመት 2012 አስቸጋሪ እንደነበር ነዉ ያመለከቱት፤


«ይህ ዓመት በተለይ በማኅበረሰባችን ለችግር ተጋላጭ ለሆነዉ ወገን በጣም ከባድ ነበር። ሆኖም ግን የችግሩን ሥረ መሠረት እየፈታን ነዉ። የመንግስት ፋይናንስ እየተሻሻለ ነዉ፤ የመወዳደር አቅማቸዉ ዝቅተኛ የሆነ ተፎካካሪዎች ይዞታ እየተሻሻለ ነዉ፤ የፋይናንስ ዘርፉ ተስተካክሏል።»
ኅብረቱ በጉባኤዉ ባንኮች ላይ በሚደረግ ቁጥጥርና በዘገየዉ ለግሪክ በሚሰጠዉ ርዳታ ላይም ተስማምቷል። ከዚህም ሌላ ኅብረቱ ፕሬዝደንት በሽር አልአሰድን ከስልጣን ለማዉረድ የሚዋጉትን የሶርያን አማፅያን በተፈለገዉ ሁሉ ለመርዳት ዝግጁነቱን ገልጿል።

የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች በነሱዉ አቆጣጠር ለ2012 የመጨረሻ ያሉትን ጉባኤቸዉን ትናንት ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ጀምረዉ ዛሬ አጠናቅቀዋል። ዛሬ የሕብረቱ ባለሥልጣናት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሪዎቹ የአዉሮጳ የምጣኔ ሐብትና የገንዘብ ቀዉስ ለማስወገድ እስካሁን ከሚከተሉት መርሕ የተሻለ ያሉትን መርሕ ቀይሰዋል።የፖለቲካ ተንታኞችና ታዛቢዎች እንደሚሉት ግን መሪዎቹ ተስፋ ከመስጠታቸዉ ባለፍ ተስማሙበት የተባለዉ አዲስ መርሕ አባል ሐገራትን የገጠመዉን ቀዉስ ለማስወገድ እስካሁን ከተወሰዱት እርምጃዎች ብዙ የሚፈይደዉ ነገር የለም።

ሥለ ጉባኤዉ ሒደትና ዉጤት የብራስልሱን ወኪላችንን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 14.12.2012
 • ቁልፍ ቃላት u
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/172pQ
 • ቀን 14.12.2012
 • ቁልፍ ቃላት u
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/172pQ