የአዉሮጳ ሕብረትና ስደተኞች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ሕብረትና ስደተኞች

ትናንት ብራስልስ-ቤልጅግ የተሠበሰቡት ሚንስትሮች በወሰኑት መሠረት የሕብረቱ አባል መንግሥታት ግሪክ፤ ኢጣሊያና ሐንጋሪ የሚገኙ አንድ መቶ ሥልሳ ሺሕ ስደተኞችን ይከፋፈላሉ።የሚንስትሮቹን ዉሳኔ ዛሬ የተሰየመዉ የመሪዎች ጉባኤ ያፀድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 16:07

የአዉሮጳ ሕብረት ሚኒስትሮች ስብስባ

የአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት የሐገር አስተዳደር ሚንስትሮች ደቡባዊ አዉሮጳ የገቡ ስደተኞችን በኮታ ለመከፋፈል በአብላጫ ድምፅ ወሰኑ።ትናንት ብራስልስ-ቤልጅግ የተሠበሰቡት ሚንስትሮች በወሰኑት መሠረት የሕብረቱ አባል መንግሥታት ግሪክ፤ ኢጣሊያና ሐንጋሪ የሚገኙ አንድ መቶ ሥልሳ ሺሕ ስደተኞችን ይከፋፈላሉ።የሚንስትሮቹን ዉሳኔ ዛሬ የተሰየመዉ የመሪዎች ጉባኤ ያፀድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጭምሮ የስደተኞች መብት ተቆርቋሪዎችን የአዉሮጳ ሕብረትን ዉሳኔ ለስደተኞቹ ችግር መፍትሔ የማይሆን በማለት እየተቹት ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic