የአኺም ሽታይነር እና የሄለን ቢሲምባ አስተያየት | የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት | DW | 01.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት

የአኺም ሽታይነር እና የሄለን ቢሲምባ አስተያየት

አኺም ሽታይነር - በናይሮቢ የተመድ የተፈጥሮ ጥበቃ መርሀግብር መሥሪያ ቤት ኃላፊ ፣ ዶይቸ ቬለ የተመድ የተፈጥሮ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ለሚያከናውነው ሳይንሳዊ ስራ ያሳየውን ትልቅ ትኩረት በዚያ የምንሰራው ሁሉ ትልቅ ትርጉም ሰጥተነዋል። ዶይቸ ቬለ መረጃዎችን ወደ ሕዝቡ ለማድረስ ረድቶናል።

እኛ የተመድ ሰራተኞች ናይሮቢ፡ ሁሉም ስው ፣ ቲምቡክቱ ይሁን በርሊን፡ ዋሽንግተን ወይም ብራዚል የሚኖሩት ሁሉ የምናቀርባቸውን መረጃዎች መልዕክት እኩል በሚረዱልን ሁኔታ ላይ ጥገኞች ነን። ዶይቸ ቬለም ሰዎች ይቀራረቡ ዘንድ ከሚረዱት መገናኛ መድረክ መካከል አንዱ ነው። ስለዚህ ዶይቸ ቬለን ለወደፊቱ ስራው መልካም ዕድል እንመኝለታለን።

------------------------

በዳሬሰላም የሰብዓዊ እና የሕጋዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል ኃላፊ- ሄለን ኪጆ ቢሲምባ

ዶይቸቬለ ፡ በተለይ የኪስዋሂሊ ቋንቋ፡ ድምፃችን እንዲሰማ ሁሌም ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮልን ቆይተዋል፤ ምክንያቱም፡ በታንዛንያ ብዙ ሕዝብ በኪስዋሂሊኛ ቋንቋ የሚሠራጨውን ዝግጅት ያዳምጣል። ይህ በጣም በጣም ጠቃሚ ነው። ሰዎች ብዙ መረጃዎችን ከዶይቸ ቬለ የኪስዋሂሊ ቋንቋ ክፍል ዝግጅት እንደሚያገኙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ሰምቻለሁ።