የአ.አ ከተማ አስተዳደር እቅድ መሸጋሸግ | ኢትዮጵያ | DW | 03.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአ.አ ከተማ አስተዳደር እቅድ መሸጋሸግ

የመስተዳድሩን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የጠቀሱ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የከተማይቱን እቅድ ማሸጋሸግ ያስፈለገው ከፌደራሉ የእድገት እና ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) እቅድ ጋር ለማጣጣም ነው ተብሏል።

Straße in Addis Abeba DW-Tage am Goethe Institut Addis Abeba, Äthiopien, alle Fotos: Reategui Die Themen: Sprache, Radio und Sprache, Sprachpolitik in Afrika, Die DW in Äthiopien, Vorstellung des Deutschkurses in Amharisch, Koproduktion mit Radio Ethiopia zum Thema Schuldenerlass, zweiwöchiger Ausbildungskurs des DWFZ für Radiojournalisten und -techniker

ይኸው ረቂቅ እቅድ አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ስልጣኑን ተረከቡ ወዲህ የመጀመሪያው የከተማይቱ መሪ እቅድ መሆኑ ነው። በኣገር ኣቀፍ ደረጃ የወጣው የፌደራሉ የእድገት እና ልውጥ (ትራንስፎርሜሽን )እቅድ የሚያበቃው እ ኣ ኣ በ 2015 ነው። የአዲስ ኣበባው የአምስት ዓመት እቅድ ደግሞ እስከ 2018 ዓጋማሽ ድረስ ይዘልቃል። ይህንኑ ለማጣጣም ነው እንግዲህ የአዲስ ኣበባ ማ/ቤት የአምስት ዓመቱን እቅድ ወደ ሁለት ዝቅ ለማድረግ የወሰነው። አዲሱ ረቂቅ እቅድም ተዘጋጅቶ ለባለስልጣናቱ መቅረቡን የአዲስ ኣበባ መስተዳድር የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምንጮች ኣስታውቀዋል።

እቅዱ አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ባለፈው ሰኔ ወር ስልጣኑን ከተረከቡ ወዲህ የመጀመሪያው የመስተዳድሩ መሪ እቅድ መሆኑ ነው። ይኸው ረቂቅ እቅድ ለከተማይቱ ም/ቤት ከመቅረቡ በፊት ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ዘልቆ ይመከርበታል ተብሎ ይጠበቃል ።

ኣሁን በተከለሰው የአምስት ዓመቱ እቅድ መሰረት ለመንገዶች ግንባታ ለውሃ ልማት እና ለመኖሪያ ቤቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት 154 ቢሊየን ብር ገደማ በጀት ተመድቦ ነበር። ወደ ተግባር ከመሄዱ በፊት ግን ከፌደራል መንግስቱ እቅድ ጋር ለማጣጣም ሲባል ባለስልጣናቱ እንደሚሉት መከለሱ የግድ ሆነዋል። በዘገባው መሰረት ከፌደራሉ እቅድ ጋር ለማጣጣም ሲባል የሚደረገው የእቅድ ማስተካከያ ግን በአዲስ ኣበባ ከተማ መስተዳድር ብቻ የተከሰተ ጉዳይ ኣይደለም። የድሬደዋ ኣስተዳደርን ጨምሮ የክልል መንግስታትም የእቅድ እና በጀት ዘመናቸውን ከፌደራሉ መንግስት መሪ እቅድ ጋር እንዲጣጣም ማድረጉ የተለመደ ነው።

A general view of the Hilton Hotel in Addis Ababa, Ethiopia, on Wednesday, March 30, 2005. Israeli ambassador to Ethiopia Doron Grossman was found shot in the head in his apartment at the Hilton in Addis Ababa, Wednesday in what appeared to be a suicide attempt, an official said. The Israeli Foreign Ministry issued a statement saying that the ambassador was gravely wounded in a shooting at his home, but said it did not appear to be a terrorist attack. (AP Photo/Boris Heger)

የመለስተኛ ጊዜ እቅዱ በኣፈጻጸም መዘግየቱ ባይቀርም የፌደራሉ መንግስት ከወዲሁ ቀጣዩን የአምስት ዓመት እቅድ መንደፍ ጀምረዋል። የኣዲስ ኣበባ መስተዳድርም ባለስልጣናቱ እንደሚሉት የአምስት ዓመት እቅዱን ወደ ሁለት ዝቅ ኣድርጎ ለመከለስ መገደዱ በዚሁ መሰረት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከፌደራሉ መሪ እቅድ ጋር ለማስታረቅ ሲል እቅዱን ሲከልስ ይህ የመጀመሪያው ኣይደለም። በቀድሞው የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ኣስተዳደር ወቅትም እንዲሁ ከ2008 እስከ2013 የነበረውን እቅድ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት በሁለት ዓመት ኣሸጋሽጎ መከለሱ ይታወሳል

ጃፈር አሊ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic