የአንጎላ ስደተኞች ከዲሞክራቲክ ኮንጎ መመለስ | አፍሪቃ | DW | 28.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የአንጎላ ስደተኞች ከዲሞክራቲክ ኮንጎ መመለስ

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የሠፈሩ እና ከአሁን ቀደም የዜግነት ጥያቄያቸዉ አጠራጣሪ በመሆኑ ወደ ሀገራቸዉ መመለስ ፈቃድ ያላገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ አንጎላዉያን ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ የሚችል ስምምነት መፈረሙ ተገለፀ።

Angola Luanda Skyline

የአንጎላ መዲና ሉዋንዳ

የዲሞክራቲክ ኮንጎ እና የአንጎላ ባለስልጣናት ይህን ስምምነት የተፈራረሙት የሁለቱ ሃገራት ባለስልጣናት በያዝነዉ ሳምንት በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ጋር ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ነዉ።
የሁለቱ ሃገራት ባለስልጣናት ኪንሻሳ ላይ የተገናኙት ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ወደ ትዉልድ ሐገራቸዉ የሚመለሱት የመጨረሻዎቹ የአንጎላ ስደተኞች የሚመለሱበትንና ከማኅበረሰቡ ጋር የሚዋሃዱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደሆነ ተመልክቶአል። የመጨረሻዉን ስምምነት ያነበቡት የኮንጎ ብሔራዊ ኮሚሽን ዶክተር ቤርተ ዚንገ እንደገለፁት ከ30 ሺሕ 600 የሚበልጡ የአንጎላ ስደተኞች በዶሞክራቲክ ኮንጎ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከል 12000 በኮንጎ የመኖርያ ፈቃድ ተሰጥቶአቸዋል። ቀሪዎቹ ግን ወደ ሀገራቸዉ ወደ አንጎላ በፍጥነት መመለስን ይሻሉ፤ ስደተኞቹን የመመለሱ ጉዳይ የዘገየዉ ቴክኒካዊ ባሏቸዉ ጉዳዮች መጓደል ነዉ።


« በትልዕኮአችን መሰረት የመጨረሻ ተመላሾችን ለመላክ በተዘጋጀንበት ወቅት አስተባባሪ የ ሰዉ ኃይል እጥረትን ጨምሮ፤ የማጓጓዣና፤ በአስቸጋሪ አየር ሁኔታ፤ የመንገድ እና በባቡር ሃዲድ መበላሸት ሁሉ ችግሮች አጋጥመዉታል»

አንጎላዉያኑን ስደተኞች የመመለስ መርሃ ግብር የተጀመረዉ የቀድሞዉ የአማፂ ቡድን የ UNITA መሪ ጆን ሳቫምቢ እንደሞቱና የአንጎላ የርስ በርስ ጦርነት እንዳበቃ በጎርጎረሳዉያኑ 2002 ነዉ። ከ 40 ዓመታት በላይ በኮንጎ የኖሩ የአንጎላ ስደተኞች በሃገራቸዉ የዜግነት መብታቸዉ ላይ ጥርጣሪ ስላላቸዉ ወደ አንጎላ መሄድን እንደማይፈልጉም ተገልፆአል። በሌላ በኩል በኪንሻሳ በተደረዉ ስብሰባ የአንጎላ የስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን አንድሪ ኩላ እንደሚሉት አንዳንዶች ለመመለስ ያልቻሉት ባልተሟላ የዜግነት መረጃ ነዉ።

« የአንጎላ መንግስት ዜጎቹን ለመቀበል ከፍተኛ ፍላጎት አለዉ ። የሆነዉ ነገር ድንበርን ለማለፍ የተፈለገዉን ነገር አልተሟላምና ነዉ። ለምሳሌ አንዳንዶች የራሳቸዉ ያልሆነ ግን የቤተዘመዶቻቸዉን ሁለት ወይም ሶስት ልጅን መያዝን ይፈልጋሉ። ወላጅ ሆነዉ ቅፁን አሟልተዉ ወደ አንጎላ መጓዝ ካልቻሉ እነዚህን ሰዎች ወደ አንጎላ እንዲገቡ አንፈቅድም፤ ምክንያቱም ይህ ህጻናትን ያካተተ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ይሆናል።»የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን ለመመለስ ያልቻሉት ስደተኞችን እንዲመለሱ ለመርዳት ቢሞክርም መረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ስደተኞቹ ያላቸዉ እጣ ፈንታ መመለስ መሆኑን በዶሞክራቲክ ኮንጎ የ UNHCR ቃል አቀባይ ሴሊነ ሽሚድት ተናግረዋል።
«በ UNHCR በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና አንጎላ ጋር በመተባበር መዝገባቸዉ የተፈተሸዉ ስደተኞች ወደ ኮንጎ ዳግም መኖርያቸዉን እንዲያመቻቹ ተጠይቀዉ ወደ« ኪምፓሴ» ወደ ተሰኘ የመሸጋገርያ ካንፕ ተልከዋል። ድንበር ተሻግረዉ ማለፍ የማይችሉት የተሟላ ማስረጃ እጃቸዉ ላይ ስላልተገኘ ነዉ፤ አንድ እና ሌላ አይነት ማስረጃ ከጠፋ ማስረጃዉን ለማግኘት እንዲያስችላቸዉ ርዳታ እያደረግን ድንበር እንዲሻገሩ እንረዳለን» ሁሉም ወገኖች ተቋርጦ የነበረዉን ስደተኞች የመመለስ ሂደት ለመቀጠል ተስማምተዋል። ይህ ስምምነት ተግባራዊ ከሆነ ደግሞ 27 ሺ ስደተኞች ወደ አንጎላ እደሚመለሱ ተመልክቶአል።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic