የአንጌላ ሜርክል የአተንስ ጉብኝት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአንጌላ ሜርክል የአተንስ ጉብኝት

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ዛሬ በግሪክ መዲና አተንስ ባደረጉት ጉብኝት ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አንቶኒስዮስ ሳማራስ ጋ ተወያዩ። ሜርክል በዚሁ ስድስት ሰዓት በቆየው ጉብኝታቸው የፊናንስ ቀውስ የገጠማት ግሪክ የጀመረችውን የተሀድሶ ሂደት አሞግሰዋል።

Greece's Prime Minister Antonis Samaras, right, and Germany's Chancellor Angela Merkel make statements to the media at the Maximos mansion in Athens, Tuesday, Oct. 9, 2012. Merkel says Greece has covered much of the ground required for recovery, during her landmark visit to the financially stricken country.(Foto:Thanassis Stavrakis, Pool/AP/dapd)

n

ግሪክ በቀጣይ ምን ማድረግ እንደሚኖርባትም ከጠቅላይ ሚንስትር አንቶንዮስ ሳማራስ ጋ መክረው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።ሜርክል ክስረት ካጋጠማት ወዲህ ግሪክን ሲጎበኙ ያሁኑ የመጀመሪያቸው ሲሆን፡ ጉብኝታቸው ሀገሩ በጀመረችው የቁጠባ ዕቅድ ከተጎዳው የግሪክ ሕዝብ ትልቅ ተቃውሞ ተፈራርቆበታል። ፖሊስ ድንጋይና ተቀጣጣይ ጓዳ ሰራሽ ፈንጂዎችን ይወረዉሩ የነበሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱም ተገልጿል። ሜሪክል ግሪክ ዉስጥ የገጠማቸዉ ተቃዉሞ ምክንያት የግሪክ መንግስት ብድር እንዲያገኝ ጥብቅ የቁጠባ ርምጃ እንዲወስድ ግፊት ማድረጋቸዉ ነዉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic