የአንጌላ ሜርክል ተፎካካሪ ማርቲን ሹልዝ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 29.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የአንጌላ ሜርክል ተፎካካሪ ማርቲን ሹልዝ

የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ በመጪው መስከረም ለሚካሔደው ብሔራዊ ምርጫ የቀድሞው የአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ማርቲን ሹልዝን እጩነት አጸደቀ።

የጀርመን ዜና አገልግሎት እና ሬውተርስ የዜና ወኪል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቅሰው እንደዘገቡት በመጪው መጋቢት ፓርቲው ማርቲን ሹልዝን በይፋ ያቀርባል። የ61 አመቱ ማርቲን ሹልዝ ለጀርመን መራሔ-መንግሥትነት አንጌላ ሜርክልን እንዲወዳደሩ 35ቱ የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ድምጽ ዛሬ ማጽደቃቸውን ሬውተርስ ዘግቧል። ማርቲን ሹልዝ ከ20 አመት በላይ በአውሮጳ ምክር ቤት አባልነት አገልግለዋል። ዛሬ በበርሊን የፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ንግግር ያደረጉት ሹልዝ በጀርመን ተፈጥሯል ያሉትን «ጥልቅ መከፋፈል» እታገላለሁ ብለዋል። ከ1000 በላይ ለሚሆኑት ታዳሚዎች ፍትኃዊ የግብር ህግጋት እንደሚሰሩም ሹልዝ ተናግረዋል። 

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ