የአንጋፋው ጋዜጠኛ ነጋሽ ገብረማርያም ቀብር ስነ ስርዓት | ኢትዮጵያ | DW | 18.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ነጋሽ ገብረማርያም ቀብር ስነ ስርዓት

አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ትላንት ሐምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ የቀብር ሥነ-ስርዓታቸው ዛሬ ከሰዓት ተፈጽሟል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:02

አንጋፋው ጋዜጠኛ ነጋሽ ገብረማርያም

አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ትላንት ሐምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ነጋሽ “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ  መታተም ከጀመረበት ጀምሮ ለሃያ ዓመት ያህል በዋና አዘጋጅነት ያገለገሉትን ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደዮሐንስን በመተካት ሁለተኛው የጋዜጣው አዘጋጅ በመሆን ሰርተዋል፡፡ የጋዜጠኝነት ትምህርታቸውን በአሜሪካ የተከታተሉት አቶ ነጋሽ የእንግሊዘኛው “ኢትዮጵያን ሄራልድ”ም አዘጋጅ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን በሥራ አስኪያጅነት መርተዋል፡፡ ከጋዜጠኝነት ሙያቸው ባሻገርም በድርሰት እና የተውኔት ስራዎቻቸውም ይታወሳሉ፡፡ የሁለት ልጆች አባት የነበሩት የአቶ ነጋሽ ገብረማርያም የቀብር ሥነ-ስርዓት ዛሬ ከሰዓት በሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በቅርብ ከሚያውቋቸው እና አብረዋቸው ከሰሩ ጋዜጠኞች ውስጥ  ላዕከማርያም ደምሴ እና ጸጋዬ ታደሰ በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል፡፡   


ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ተስፋለም ወልደየስ

አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic